Page 86 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 86
አብን
ከዘመናዊ የኢኮኖሚ ክፍሉ ጋር የሚተሳሰርበት ስልት
እንዲቀየስ ልዩ ትኩረት ይሰጣል፡፡ የገጠር አካባቢዎች
ከቢሮክራሲያዊ ተፅዕኖ ውጭ ራሳቸውን በራሳቸው
የሚመሩበት የኢኮኖሚ አስተዳደር፣ የህግ የበላይነት
የሚከበርበት እና የዜግነት የሃላፊነት ስሜት እንዲኖራቸው
በገጠር ስለግብርና ጥሩ እውቀት ያላቸውና፣ የገጠርን ኑሮ እና
ነዋሪዎችን የሚወዱ የኢክስቴንሺን አገልግሎት ሰራተኞች
በከፍተኛ ቁጥር እንዲሰለጥኑ ይደረጋል፡፡
የአጠቃላይ ኢኮኖሚው (Macro Economy) ቁጥጥር የተሻለ
እንዲሆን አዳዲስ ዘዴዎችን እናስተዋውቃለን፡፡ የኢኮኖሚው
እንቅስቃሴ ከሀገራዊ የልማት ትልም አንፃር እንዲቃኝ፣ የበጀት
(Fiscal) ፣ የገንዘብ (Monetary) የኢንዱስትሪ እድገት እና
የአካባቢ (Regional) ልማት ፓሊሲዎች እርስ በርስ የተናበቡ
እንዲሆኑ እንጥራለን፡፡
የሸማቹ የፍጆታ አቅም እንዲበረታታ፣ ለኢኮኖሚ እድገት
ፍጆታ መሰረታዊ ሚና እንዲጫወት የሚያደርጉ የፖሊሲ
አቅጣጫዎችን እንዲቀየሱ እናደርጋለን፡፡ በተመሳሳይ መልኩ
በኢንቨስትመንት እና በፋይናስ ዘርፍ የሚደረጉ ለውጦች
(Reform) በአቅርቦቱ ሰንሰለት /Supply chain/
ኢንቨስትመንት የጎላ ሚና እንዲኖረው በዚህ ሂደትም አዲስ
የሥራ መስክ (employement) እንዲፈጠር እንጠራለን፡፡
የሀገሪቱ የታክስ ስርዓት እንዲለውጥ የየአካባቢው የታክስ
ስርዓት እንዲሻሻል፣ የኢኮኖሚው የፋይናስ ዘርፍ ኢኮኖሚውን
በተገቢው ሁኔታ እንዲያቀላጥፍ እና እንዲያበረታታ
በሚያስችል መልኩ እንዲለውጥ እናደርጋለን፡፡ ኢኮኖሚው
84 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !