Page 51 - DINQ MAGAZINE SEPTEMBER 2020 EDITION
P. 51

መስከረም የወራቱ ጌታ


                                     በሔኖክ ያሬድ


         ‹‹ኢዮሃ አበባዬ . . . መስከረም ጠባዬ››         የሚጀምሩበት፣ ሜዳዎችና ተራራዎች                  እንግጫ ነቀላ ዘመን ሲለወጥ የሚከወን
         ዘመን በተሞሸረ ዓመት በተቀመረ ቁጥር ሰው           ሸለቆዎችም በአበባ የሚያሸበርቁበትና                ባህላዊ ሥርዓት ነው፡፡ በዋዜማው ያላገቡ
         መልካም ምኞት የሚለዋወጥበት ሐረግ                የሚቆጠቆጡበት ነው ይሉታል፡፡                    ሴቶች ወደ መስክ ወርደው እንግጫ
         ነው፡፡ ድምፃውያንም ያቀነቅኑታል፡፡               እንዲህም በመሆኑ የጨለማ የችግርና የአፀባ            ይቆርጣሉ፡፡ ምሽቱን ደግሞ እንግጫውን
         እንግዲህ ኃያሉ ክረምት ሊያበቃ፣ መሰስ እያለ         ጊዜ የሚያበቃበት የብርሃን፣ የደስታ የሸት፣           ሲጎነጉኑ ይቆያሉ፡፡ ሲነጋ ደግሞ በጠዋት
         ወጥቶ ለከርሞ ሊመለስ ከመስቀል በዓል              የፍሬና የጥጋብ ጊዜ የሚጀምርበትና                 ተጠራርተው በመሰባሰብ በየሰው ቤት እየዞሩ
         በኋላ አንድ ሳምንት (መስከረም 25 ቀን            የሚተካበት ነው ብሎ ሕዝቡ                      የተጎነጎነው እንግጫ ከቤቱ ምሰሶ ላይ
         2011 ዓ.ም.) ቢቀረው ነው፡፡ በመጻሕፍት          ስለሚያምንበትም የዕንቁጣጣሽ በዓልን                ያስራሉ፡፡ እንግጫ የአዲስ ዓመት የምሥራች
         እንደተጠቀሰው፣ ኢዮሃ አበባዬ የደስታ ቃል           ከሁሉ አብልጦ ግምት ስለሚሰጠው በእሳት              ምልክት ነው፡፡ እንግጫ ከአዲስ ዓመት
         ነው፡፡ ወንዶች የደመራ ለት እየዘፈኑ ድምሩን         ብርሃንና በእሳት ቡራኬ በየቤቱ እንደ               ማብሰሪያ በተጨማሪ የመተጫጫ በዓልም
         የሚዞሩበት ያበባ ዘፈን ነው፡፡ ሰኔ ግም ብሎ፣        ሁኔታው እንስሳ አርዶ ደም አፍስሶ                 ጭምር ነው፡፡
         ያምሌን ጨለማ አልፎ፣ የነሐሴን ጎርፍ              ይቀበለዋል፡፡ ያከብረዋል ሲሉም
         ሙላትን በእኝኝ ተሻግሮና ተንተርሶ                አክለውበታል፡፡                             እንግጫው ነቀላ በዜማ የታጀበ ነው፡፡
         በጠንካራው ዝናብ (ውሃ) ምክንያት ብቅ             በመምህር ዓለሙ ኃይሌ አገላለጽ በወርኃ              ‹‹እቴ አበባዬ ነሽ
         የምትለዋ ያደይ አበባ ናትና፤ ውሃ ያደረገውን         መስከረም መሬቷ በአደይ አበባ አሸብርቃ              አደይ ተክለሻል
         ታምር፣ ያስበቀለውን አበባ አደያዊን               ስለምትታይና በተለይም ዕንቁ የመሰለ አበባ            አደይ ተቀምጠሻል
         ተመልከት ለማለት ‹‹ኢዮሃ አበባዬ                ስለምታወጣ መሬቷን ዕንቁጣጣሽ፣ ዕንቁ               ባሶና ሊበን
         መስከረም ጠባዬ›› ይባላል፡፡                   የመሰለ አበባ አስገኘሽ ለማለት ዕንቁጣጣሽ            አዋጋው ብለሻል
         ታዋቂው ደራሲ በዓሉ ግርማ ‹‹ደራሲው››            ተብላለች፡፡ አያይዘው አቧራ፣ ቡላ የነበረው           ቦሶና ሊበን
         በተሰኘው ልቦለዱ የመስከረምን ድባብ               መሬት በዝናቡ ኃይል ለምልሞ ተመልከቱኝ፣             ምነው ማዋጋትሽ
         የገለፀበት አገላለጹ አዲሱ ዓመት በመጣ             ተመልከቱኝ የምትል ያሸበረቀች፣ አበባ               አንዱ አይበቃም ወይ››
         ቁጥር ሁሌ የሚታወስ ነው፡፡ ‹‹መስከረም            የተንቆጠቆጠች ሆነች የሚል ለዕንቁጣጣሽ              በዚህ ጊዜ ወንዶች ደግሞ ያዘጋጁትን ዳቦት
         ጠባ፡፡ የመስከረም ጮራ ዕንቁጣጣሽ ብላ             ስያሜ መነሻ ሊሆን እንደሚችል ይጠቁማሉ፡፡            (የችቦ ስም) በእሳት ለኩሰው እያበሩ
         ተግ አለች፡፡ ልጃገረዶች ሳዱላቸውን                                                     በመምጣት እንግጫ ለሚጎነጉኑት ሴቶች
         አሳመሩ፡፡ አደስ ተቀቡ፡፡ እንሶስላ ሞቁ፡፡          አብሣሪው እንግጫ                            ያበሩላቸዋል፡፡ ዳቦታቸውን እያበሩ ወደ
         ወንዝ ወረዱ፡፡ ቄጤማ ለቀሙ፡፡ ፀአዳ              እንግጫ የሣር ዓይነት ነው፡፡ በአዲስ ዓመት           ሴቶቹ በሚያመሩበት ጊዜ የሚያዜሙት ዜማ
         ልብሳቸውን ለብሰው፣ አሽንክታባቸውን               ዋዜማ ልጃገረዶች መስክ ወርደው                   አላቸው፡፡
         አጥልቀው፣ ‹አበባዬ ሆይ - ለምለም› በማለት         የሚነቅሉት ነው፡፡ የዕንቁጣጣሽ ብሥራት              ‹‹ኢዮሃ ኢዮሃ
         ተሰብስበው ብቅ አሉ - እንደ ጮራይቱ፡፡            ነጋሪ ነው፡፡ ‹‹በሰሜን ሸዋ በምሥራቅና             የቅዱስ ዮሐንስ
         የወርሀ መስከረም ብሩህ ተስፋና ስሜት              ምዕራብ ጎጃም ዞኖች የተመዘገቡ                   የመስቀል የመስቀል
         በምድሪቱ አስተጋባ፡፡ ጠፍ እያለ መጣ              የኢንታጀብል ባህላዊ ቅርሶች›› መድበል ላይ           አሰፉልኝ ሱሪ
         ምድሩ፡፡ ወንዙም እየጠራ፡፡ ኩል መሰለ             ስለ እንግጫ እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡              ኢዮሃ›› በማለት ያዜማሉ፡፡
         ሰማዩ፡፡ ሜዳው፣ ጋራው፣ ሸንተረሩ ወርቃማ           በዘመን መለወጫ ዋዜማ እንግጫ ሳር                 በከተሞች አካባቢ እንግጫ ነቀላው እየቀረ
         የአደይ አበባ ካባ ለበሰ፡፡ ደመራ ተደመረ፡፡         በልጆች እየተነቀለ እንደቋጨራ እየተጎነጎነ            አበባዮሽ የሚለው ጨዋታ በመስፋፋት ላይ
         ተቀጣጠለ ችቦ፡፡ ‹ኢዮሃ አበባዬ - መስከረም         ጣራ ላይ ተወርውሮ ያድርና ጠዋት ላይ               ይገኛል፡፡ ልጃገረዶቹ ወደየሰው ቤት ሲሄዱ
         ጠባዬ› ተባለ፡፡››                         ለዘመን መለወጫ እየተጎነጎነ ራስ ላይ፣ ቡሃቃ          ሎሚ ይሰጣቸው የነበረ ሲሆን፣ አሁን ላይ
         ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ ጥያቄዎችና ባሕሎች››           አንገት ላይና ሌማት ክዳን ላይ ይታሰራል፡፡           ግን የእንግጫው ሴቶች ራሳቸው ‹‹እንኳን
         በተሰኘው የሀብተማርያም አሰፋ (ዶ/ር)             ቡሃቃ እና ሌማት ላይ የመታሰሩ ምልክትነት            አደረሳችሁ›› እያሉ ሎሚ ሲሰጡ ገንዘብ
         መጽሐፍ መስከረምን እንዲህ ገልጸዋታል፡፡            ለረድኤትና ለበረከት ሲባል የሚደረግ ነው፡፡           ይሰጣቸዋል፡፡
         መስከረም ‹‹ምስ-ከረም›› ከከረመ በኋላ            ራስ ላይ የታሰረው ደግሞ ለመስቀል በዓል
                                              ተቀምጦ ይቆይና ደመራው ላይ ይታሰርና
         ወይም ክረምት ካለፈ በኋላ ማለት ነው፡፡            እንዲቃጠል ይደረጋል፡፡ ለራስ ምታትና               እንግጫ ከአዲስ ዓመት ማብሰሪያ በተጨማሪ
         የመስከረም ወር ዝናብ የሚቆምበት ፀሐይ             ለጤንነት ሲባል በማኅበረሰቡ የሚከወን               የመተጫጫ በዓልም ጭምር ነው፡፡
         የምትወጣበት ወንዞች ንጹሕ ውሃ ጽሩይ ማይ           ነው፡፡                                  ልጃገረዶች እንግጫውን እየነቀሉ
         የሚጎርፍበት፣ አፍላጋት የሚመነጩበት፣                                                    የሚያዜሙት ዜማ ይህንኑ ይጠቁማል፡፡
         አዝርዕት ማለት የተዘሩት አድገው ማሸት
                                                                                                        ወደ ገጽ  61 ዞሯል

           DINQ MEGAZINE      September 2020                                           STAY SAFE                                                                                     51
   46   47   48   49   50   51   52   53   54   55   56