Page 27 - Descipleship 101
P. 27

ሁለቱ ተፈጥሮዎች
ለማደግና በክርስትና ህይወት ውስጥ ለውጥ ለማየት ክርስቲያን ሁለት አይነት ተፈጥሮ እንዳለው ሊያውቅ ያስፈልጋል። በዚህ አለም ስንወለድ አዳማዊና የሆነ አሮጌ ተፈጥሮ ይዘን እንመጣለን። በሌላ አባባል ስጋ ለብሰን እንወለዳለን። በክርስቶስ አምነን ዳግመኛ ስንወለድ ደግሞ አዲሱን ተፈጥሮ እንቀበላለን ወይንም አዲስ መንፈስ እንቀበላለን። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ (በዮሐ.3፡6) እንደተናገረው “ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው”።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ስጋ” ሁለት አይነት ትርጉም አለው። አንደኛው የተፈጥሮ ሰውነታችን (ዮሐ.3፡6) ሲሆን ሌላው ደግሞ አሮጌው ባህርይ (እኔነት) ማለትም ከአዳም የወረስነው አሮጌ ባህርይ ነው። መንፈስ የሚለው ቃል የሰውን መንፈስ ያሳያል። ማንኛውም ሰው መንፈስ ነፍስና ስጋ አለው (1ተሰ.5፡23)። አዲሱ ተፈጥሮአችን ከስጋ ተቃራኒ በመሆኑ መንፈስ ተብሎ ይጠራል።
“የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችንን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ስጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።”
የሚከተለውን ሰንጠረዥ ስትመለከት ሁለቱን የሰው ተፈጥሮዎች ልዩነት ለማስተዋል ሞክር።
  26





























































































   25   26   27   28   29