Page 28 - Descipleship 101
P. 28

  ስጋ መንፈስ
   ከስጋ የተወለደ ስጋ ነው (ዮሐ. 3፡6)
   ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው (ዮሐ.3፡3)
 አሮጌው ሰው (ኤፌ.4፡22) አዲሱ ሰው (ኤፌ.4፡24)
   በኃጢያት ህግ የሚማረክ (ሮሜ. 7፡23)
  በእግዚአብሄር ህግ ደስ ይለዋል (ሮሜ.7፡22)
      ከአለም ጥፋት ያመለጠ (2ጴጥ.1፡4)
 እነዚህ ሁለት ተፈጥሮዎች እርስ በርሳቸው ይዋጋሉ። አሮጌው ተፈጥሮአችን የሚፈልገውን ነገር አዲሱ ተፈጥሮአችን በፍጹም አይፈልገውም። የሁለቱ ባህሪ እጅግ የተለያየና የማይገባባ በመሆኑ እነዚህ ተፈጥሮዎች እርስ በርሳቸው ጠላቶች ሆነው ይኖራሉ። ከዚህም የተነሳ የምንውደውን ልናደርግ አንችልም (ገላ.5፡17)።
“ስጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በስጋ ላይ ይመኛልና፤ እነዚህም አርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም”
ብዙ አዲስ አማኞች ስጋ ምን እንደሆነ፤ አዲስ ህይወትም ምን እንደሆነና ድልን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ባለማወቃቸው ምክንያት በክርስትና ሕይወታቸው ድልን አይለማመዱም። እስቲ የእግዚአብሄር ቃል ስለእነዚህ ነገሮች ምን እንደሚል እንመልከት።
27
























































































   26   27   28   29   30