Page 30 - Descipleship 101
P. 30

መሆኑን ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ በስጋ ተነሳስተን ምንም ነገር እንዳናደርግ እንዲህ ሲል ይነግረናል፦
”ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ ክርስተስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለስጋ አታስቡ። ” ሮሜ. 13፡14
ዳግመኛ ከተወለድን በኋላ አሮጌው ስጋ ከእኛ ጋር ባይኖር ኖሮ እንዲህ ባላለ ነበር። ደህንነት ካገኘን በኋላም አሮጌ ስጋችን የተሻለ አይሆንም። ስጋ ማፍራት የሚችለው ስጋ ነው (ዮሐ.3፡6)። ወደ ሌላ አዲስ ፍጥረት ሆነ ወደ ተሻለ ነገር አይለወጥም፤ የእግዚአብሄር ጠላትም ሆኖ ግን ይኖራል (ሮሜ.8፡7)።
ሰው ዳግመኛ ከተወለደ በኋላ የልቡን ክፋት መረዳት ይጀምራል። ይኸውም መንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ ሆኖ የስጋን ክፋት ስለሚያጋልጥ ነው። ክርስቲያንም ከጌታ ጋር ብዙ ከቆየም በኋላ ምንግዜም አሮጌ ስጋው ከማያምን ሰው ባልተሻለ መንገድ ርኩስ እንደሆነ ይረዳል።
የአሮጌው ሰው ባህሪ ምናልባት ለየት ባለ አይነት ይገለጥ ይሆናል ነገር ግን አሁንም ያው ራሱ አሮጌው ሰው ስጋ ነው።. ሁለቱ የአብርሃም ልጆች የሁለቱ ተፈጥሯችን ምሳሌዎች ናቸው። እስማኤል አሮጌውን ሰው ሲወክል፤ ይስሐቅ ደግሞ አዲሱን ሰው ይወክላል። እስማኤል በቤት ውስጥ አስቸጋሪ ሰው አልነበረም። ነገር ግን ይስሐቅ ሲወለድ የእስማኤል እውነተኛ ተፈጥሮ ብቅ አለ፤ ብጥብጥ ተጀመረ (ዘፍ.21፡9)። አዲሱን ሰው እስካላገኘን ድረስ
29





























































































   28   29   30   31   32