Page 32 - Descipleship 101
P. 32
ይህ በማንኛውም ሰው ዘንድ አውነት ነው መንፈሳዊ ለሆኑት ለጥቂቶችም ብቻ አይደለም (1ዮሐ.2፡1)። ነገር ግን በኃጢያት ውስጥ አይመላለስም፤ የበለስ ዛፍ ማፍራት የሚችለው የበለስ ፍሬ ብቻ ነውና።
“ወንድሞች ሆይ፤ በለስ ወይራን ወይስ ወይን በለስን ልታፈራ ትችላለችን? ከጨው ውሃም ጣፋጭ ውሃ አይወጣም። ” (ያዕ.3፡12)
በዚህ አይነት በእኛ ውስጥ ያለው ቅዱሱ መንፈስ የሚያፈራው መልካሙን ብቻ ነው። የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከትና አነጻጽራቸው።
“በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም።”
ሮሜ 8፡8
“ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ
ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥
ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን
ሊያደርግ አይችልም።” 1ዮሐ.3፡9
እንደ 1ዮሐ. 3፡9 አባባል የማይቻለው ምንድነው? እንደ ሮሜ.8፡8 አባባል የማይቻለው ምንድንነው?
3. አዲሱን ተፈጥሮ የእግዚአብሄር ነገር ደስ ያሰኘዋል።
ሁለቱም ተፈጥሮዎች በተፈጥሮና በባህርያቸው የተለያዩ ስለሆኑ የሚወዱትም የተለያየ ነገርን ነው። ለምሳሌ አዲሱ ሰው መልካም 31