Page 34 - Descipleship 101
P. 34

መጽሐፍ ቅዱስ የስጋን ፈቃድ እንድናደርግ፤ ብናደርግ ኃጢያተኛ ተፈጥሮአችንን እንጂ አዲሱ ተፈጥሮ ደስ እንደማያሰኝ ይነግረናል።
 “ 8፡13
ሮሜ.
እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ
 ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ።”
ጳውሎስ በሮሜ መልዕክቱ የሚያስተምረው የራስን ስጋዊ ህይወት ስለማጥፋት ሳይሆን የአሮጌውን ተፈጥሮ ስራ መግደል እንዳለብን ያስተምራል። “መግደል” ሲል በራሳችን የስጋ ፈቃድ ላይ እውነተኛ ዳኝነትን ማድረግ ወይንም የስጋን ፍላጎት እንቢ ለማለት አቅም ማግኘት ማለት ነው። በራሳችን የስጋ ፈቃድ ላይ እና በኃጢያት ላይ እንቢ ብለን እርምጃ ስንወስድ እግዚአብሔር የሚከብርበትን ህይወት እየተራመድን የድል ህይወትን እንለማመዳለን (1ቆሮ. 11፡31)። በኢያሱ ምዕራፍ አምስት እንደተጠቀሰው ታሪክ እስራኤላውያን ከነዓንን ከመውረሳቸው በፊት የተሳለ ቢላዋ በራሳቸው ላይ ማሳለፍ (ግርዘት ማድረግ) ነበረባቸው። ይህን የተሳለ ቢላዋ በጌልጌላ ተጠቀሙበት። ስፍራውም የድል አድራጊዎች ማደሪያ (camp) ሆነ (ኢያሱ 5፡2፤3፡9፤ 10፡23)። ይህ አንድ በራሱና በኃጢያቱ ላይ የሚፈርድ ድልም በሕይወቱ ያለን የክርስቲያን ህይወት ይመስላል፤ ይህንንም ማድረግ የምንችለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ብቻ ነው።
33




























































































   32   33   34   35   36