Page 36 - Descipleship 101
P. 36

ክርስቶስ ስራውን ስለእኛ ስለስራ አሁን ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ስራውን ይሰራል። ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
መንፈስ ቅዱስ ስብዕና አለው (He is a person)
መንፈስ ቅዱስ ኀይል ሳይሆን ዘላለማዊ፣ ከአብና ከወልድ ጋር እኩያ መለኮት ነው። በሌላ አነጋገር መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሄር ነው (ማቴ. 28። 19፤ 2ቆሮ. 13፡14፤ ዕብ. 9፡14)። መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ለመሆኑ አመልካች የሆኑ የእግዚአብሄር መለኮታዊ ባህሪያት አሉት።
§ መንፈስ ቅዱስ ፈጣሪ ነው - ዘፍጥ1፣1-3፤ ኢዮብ33፣4
§ መንፈስ ቅዱስ ሁሉን ይችላል - ሉቃ1፣35-37፤ ኢዮብ33፣4 § መንፈስ ቅዱስ በሁሉ ሥፍራ በአንድ ጊዜ ይገኛል -
መዝ139፣7-10
§ መንፈስ ቅዱስ ሁሉን አዋቂ ነው - ሮሜ8፣26-27 § መንፈስ ቅዱስ ዘላለማዊ ነው - ዕብ.9፣14
የሚከተሉትን ጥቅሶች ስለ መንፈስ ቅዱስ ምን ያስተምሩሃል? በቀኝ በኩል ባለው ክፍት ቦታ ላይ ጻፍ።
ማቴ.12፡28------------------------------------------------------ 1ቆሮ.2፡10------------------------------------------------------- መዝ. 139፡7-10-------------------------------------------------
 35

























































































   34   35   36   37   38