Page 35 - Descipleship 101
P. 35
መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ውስጥ
በአሮጌው ተፈጥሮ ላይ ድል እንደምናገኝ የሚረዱንን የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልክተናል፦
ፊ.ል.3፡3 ሮሜ.13፡14
ሮሜ.8፡13
እስቲ እንደገና አንብባቸውና ስለ መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሚናገሩ አሰላስል። እንደ ክርስቲያን መንፈሳዊ ኑሮን መኖር እንድንችል ሃይል የሚሰጠን መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። እግዚአብሄር ኃጢያያታችንን ይቅር እንዳለልን በማወቅ ብቻ ፈተናን እንድናልፍና በኃጢአት ላይ ድል ተቀዳጅተን እንድንችል አያደርገንም። ድል ለማግኘት አሁን በሰማያት ከብሮ ካለው ከኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ እርዳታ ያስፈልገናል።
መድኀኒታችን ስለእኛ ኀጢያት በመስቀል ላይ ቅጣትን ከተቀበለ በኋላ ከሞት ድል አድርጎ በሦስተኛው ቀን ተነስቷል። አይኖቻችንን ወደ ኢየሱስ ስናነሳ መንፈስ ቅዱስ ከኀጢአት ኃይል ነጻ ያወጣናል። 34
“እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም
የምንመካ በሥጋም የማንታመን እኛ የተገረዝን ነንና።”
“ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም
እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ።”
“እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን
የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ።”