Page 33 - Descipleship 101
P. 33
የሆኑ ነገሮችን፤ እግዚአብሄር የሚደሰትበትንና ራሱም የሚታነጽበትን ለይቶ ይመርጣል። አዲሱ ሰው ከሚያስደስቱ ነገሮች በጥቂቱ ብንዘረዝር፤ እግዚአብሄርን መታዘዝ፣ እግዚአብሄርን ማምለክ፣ ቅዱሳንን ማገልገል፣ ከኃጢአት መራቅ፣ ጽድቅን ማድረግ፣ ስለክርስቶስ መመስከር፣ ከእውነት ጋር መስማማት፣ ፈቃዱን ለመንፈስ ቅዱስ ማስገዛትና ሌሎችም ብዙ መንፈሳዊ ነገሮችን ይወዳል። አሮጌው ሰው ደግሞ ከዚህ ተቃራኒውን ይወዳል። ይህን ደግሞ በአዲሱ ተፈጥሮ የተወደደ አይሆንም። (ሮሜ. 7፡22፤ ሐዋ.9፡11፤ 1ጴጥ.2፡2፤ 1ዮሐ.3፡14)
ክርስቲያን ድልን እንዴት ያገኛል?
ሁለት አይነት ክርስቲያኖች አሉ፤ የመጀመሪያዎቹ አሮጌው ተፈጥሮ የሚላቸውን የሚያደርጉ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ አዲሱን ተፈጥሮ የሚታዘዙ ናቸው (1ቆሮ.3፡1-4) እና 2፡15)። ጳውሎስ በልጵስዮስ 3፡3 ላይ በስጋም ሆነ ማድረግ በምንችለው ነገር ላይ መደገፍ እንደሌለብን ይነግረናል። ስጋ ክፉ ስለሆነ እግዚአብሄርንም ሊያስደስት አይችልም።
“
ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ
አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ።በቀን እንደምንሆን
በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና
በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤ ነገር ግን ጌታን
ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ
አታስቡ።” ሮሜ 13፡12
32