Page 31 - Descipleship 101
P. 31
አሮጌው ሰው አይጣላንም፤ ነገር ግን አዲሱን ሰው ያገኘን ጊዜ በአብርሃም ቤት እንደሆነው ጦርነት ተጀመረ ማለት ነው።
አዲሱ ተፈጥሮ
“ከእግዚአብሄር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፤ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሄር ተወልዶአልና ኃጢዓትን ሊያደርግ አይችልም። ” (1ዮሐ. 3፡9)
የእግዚአብሄር ተፈጥሮ (ባህሪ) በውሥጡ ስላለ እውነተኛ ዳግመኛ የተወለደ ሰው በየቀኑ በድፍረት ኀጢዓት አይመላለስም። ያለምንም ጸጸት ኃጢዓትን እየተለማመድ እንደቀደመው አሮጌ ሕይወቱ መመላለስ አይችልም። ዳግም ሲወለድ በውስጡ የቅድስና መንፈስ ስለሚያድር በድፍረት ኃጢያት ውስጥ መኖር አይቀጥልም። ስለ አዲሱ ተፈጥሮ እነዚህን ሶስት ነገሮች አስተውል፤
1. አዲሱ ተፈጥሮ ከእግዚአብሄር የመጣ ነው፤
በዚህ አለም ስንወለድ የአዳምን ተፈጥሮ ይዘን እንደምንመጣ ዳግመኛ ስንወለድ ደግሞ አዲሱን ተፈጥሮ ከጌታ እንቀበላለን። የአሮጌው ሰው ባህሪ በአጠቃላይ መጥፎ ሲሆን የአዲሱ ተፈጥሮ ባህሪ ግን ሙሉ በሙሉ መልካም ነው፤ መለኮታዊ ተፈጥሮ (ባህሪ) እየተባለም ይጠራል (2ጴጥ1፡4)።
2. አዲሱ ተፈጥሮ ኃጢያት ሊሰራ አይችልም (1ዮሐ.3፡9፣ 5፡18)
30