Page 6 - Descipleship 101
P. 6

መግቢያ
በሰለጠነውም ሆነ አልሰለጠነም በሚባለው አለም ቤት ሲሰራ የሚጀመረው ከመሰረት ነው። መሰረቱ ያልተስተካከለ ቤት ይጣመማል፤ ይወድቅማል። መሰረቱ በትክክል ያልተሰራ ቤት የመሬት መንቀጥቀጥ ወይንም የውሃ መጥለቅለቅ ሲመጣ ይጣመማል ወይም ይወድቃል። በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ፎቅ ቤት ርዝመቱና ክብደቱ የሚወሰነው በመሰረቱ ጥንካሬ ነው። የአማኝ መንፈሳዊ መሰረት መንፈሳዊ እድገቱን ይወስነዋል።
መሰረታዊ የደቀ መዝሙር ትምህርትን መማር ሕይወታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንዲመሰረት ያደርገዋል። ብዙዎች ኢየሱስ ክርስቶስን የህይወታቸው አዳኝ አድርገው ከተቀበሉ በኋላ ያለምንም ተከታይ የወንጌል ትምህርት መንፈሳዊ ጉዟቸውን ሊቀጥሉ ሲሞክሩ በሀጢያትና በሰይጣን ፈተና ተሰነካክለው ይወድቃሉ። ቢጸኑ እንኳን ህይወታቸውም ከቀደመው የጨለማ አኗኗር ዘዬ መላቀቅ የሚችሉበት የደቀመዝሙር ትምህርትን ስላልተማሩ ከአለማዊት ያልተላቀቀ ህይወት እየኖሩ በእግዚአብሄር ቤት ይመላለሳሉ።
አዲስ አማኞች በወንጌል ስር ሰደው እንዲያድጉ መሰረታዊውን የደቀ መዝሙር ትምህርት ሊማሩ ይገባቸዋል። የቤተክርስቲያን አገልጋዮችም ይህንን በሚገባ ተረድተው ጌታን የተቀበሉትን አማኞች በቶሎ በወንጌል መሰረት ላይ ሊመሰርቷቸው ይገባል።
5






























































































   4   5   6   7   8