Page 7 - Descipleship 101
P. 7
ይህ መሰረትን የመትከል ወንጌል ብዙ ትጋት የሚጠይቅና ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆንም አማኝ በአለት ላይ እንደተሰራ ቤት በወንጌል እውነት ላይ ተደላድሎ ፍሬና ሆኖ ስናይ እጅግ የሚያስደስትና ከጌታ ዘንድ የአክሊል ሽልማት የሚያሰጥ አገልግሎት መሆኑን ተረድተን በትጋት ልንበረታታ ይገባል።
በጥሩ የወንጌል መሰረት ላይ የተመሰረተ አማኝ በየዘመኑ በሚነሳው የተለያየ አይነት ሰይጣናዊም ሆነ ሰብአዊ ፍልስፍና አይፍገመገምም። ሰይጣናዊ የስደት ወጀብም ቢነሳ መሰረቱ በወንጌል ላይ የተመሰረተ አማኝ እጁን አይሰጥም። ይህንን በመመልከት ይህች ትንሽ መጽሀፍ በውስጧ አስራ ሁለት መሰረታዊ የክርስትናን ትምህርት ማንኛውም ሰው ሊረዳው በሚችለው ቀላል ቋንቋ ይዛ ቀርባለች። ጌታ ኢየሱስ ሁለቱን አሳና አምስቱን እንጀራ ባርኮ ለብዙ ሺህ ሰዎች በረከት እንዳደረገ፤ ይህች ታናሽ መጽሀፍ ለብዙዎች ጤነኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሰረት መጣያ አድርጎ እንዲጠቀምባት ጸሎቴ ነው።
ፓስተር አስፋው በቀለ በሻህ
6