Page 8 - Descipleship 101
P. 8

እምነት
በክርስትና ህይወት ውስጥ እንድናድግ የሚረዱንን ታላላቅ እውነቶች ቀላልና ግልጽ በሆነ መንገድ በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ለማብራራት እንሞክራለን። ጴጥሮስ ሰለ እነዚህ እውነቶች ሲናገር ልክ እንደ ንጹህ ወተቶች ናቸው ይላል።
ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደሆነ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደተወለዱ ሕጻናት ተንኮል የሌለበትን የቃሉን ወተት ተመኙ። (1ኛጴጥ.2፡2)
እውነተኛ ክርስቲያን (አማኝ) ከእግዚአብሄር ቃልና ከመንፈስ ቅዱስ ተወልዶ የእግዚአብሄር ቤተሰብ አባል የሆነ ሰው ነው (1ጴጥ.1፡23)።
“ኢየሱስም መለሰ እንዲህ ሲል፡- እውነት እውነት እልሃለው ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሄር መንግስት ሊገባ አይችልም።” (ዮ.3፡5)
ዳግም በተወለድን ጊዜ በመጀመሪያ እንደ ሕጻናቶች ብንሆንም ነገር ግን እንድናድግ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን እንድንደርስ የእግዚአብሄር አላማና ፈቃድ ነው።
“ልጆች ሆይ ሃጢያታችሁ ስለ ስሙ ተሰርዮላችኋልና እጽፍላችኋለሁ። አባቶች ሆይ ከመጀመሪያ የነበረውን
አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጎበዞች ሆይ ክፉውን አሸንፋችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ልጆች ሆይ አብን አውቃችኋልና
7


























































































   6   7   8   9   10