Page 10 - Descipleship 101
P. 10
ጤነኛ የሆነ እምነት እንዳለ ስህተት የሆነ (የተዛባ) የእምነት ትርጉም አለ። አንድ ሰው ስለአንድ ነገር እውነትነት ሊረዳ ይችላል ነገር ግን እንደተረዳነው እውነት ካልተራመደ ይህ ሰው እውነትን ተረድቷል ወይም እምነት አለው ማለት አንችልም። ለምሳሌ፡- ንጉስ አግሪጳ ጳውሎስ የሚሰብከውን በመደነቅ ይሰማው ነበር፤ ነገር ግን ጌታ ኢየሱስን የህይወቱ አዳኝ አድርጎ አልተከተለውም (ሐዋ.26፡27)። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ የሰሙትን ሁሉ ያምናሉ፤ ሌሎች ደግሞ ባይገባቸውም በሚያስደንቃቸው ነገር ሁሉ ያምናሉ። ይህ ትክክለኛ ጤነኛ ያልሆነ እምነት ነው።
እምነት ምንድነው?
“እምነት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው”። (ዕብ. 11፡1)
አንድ ሰው እምነትን ለማግኘት፡-
• በመጀመሪያ እግዚአብሄር ራሱን ለሰው ልጆች በክርስቶስ መግለጡን ማመን አለበት፤
• የሚቀጥለው ደረጃ ከዚህ እውነት ጋር መስማማትና ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ መቀበል ነው። ሰው እግዚአብሄር እራሱን በክርስቶስ ኢየሱስ ለሰው ልጆች መግለጡን ሊያምን ይችላል ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስን ካልተቀበለ ደህንነትን ፈጽሞ ሊያገኝ አይችልም።
9