Page 12 - Descipleship 101
P. 12
2. ጳውሎስ (ሐዋ. 27፡21-25)
“ሳይበሉም ብዙ ቀን ከቆዩ በኋላ፥ ያን ጊዜ ጳውሎስ በመካከላቸው
ቆሞ እንዲህ አለ። እናንተ ሰዎች ሆይ፥ ሰምታችሁኝ በሆነ ኖሮ
ከቀርጤስ እንዳትነሡ ይህንም ጥፋትና ጕዳት እንዳታገኙ ይገባችሁ
ነበር። አሁንም። አይዞአችሁ ብዬ እመክራችኋለሁ፤ ይህ መርከብ
እንጂ ከእናንተ አንድ ነፍስ እንኳ አይጠፋምና። የእርሱ የምሆንና
ደግሞ የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ በዚች ሌሊት
በአጠገቤ ቆሞ ነበርና፥ እርሱም። ጳውሎስ ሆይ፥ አትፍራ፤ በቄሣር
ፊት ልትቆም ይገባሃል፤ እነሆም፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር
የሚሄዱትን ሁሉ ሰጥቶሃል አለኝ። ስለዚህ እናንተ ሰዎች ሆይ፥
አይዞአችሁ፤ እንደ ተናገረኝ እንዲሁ እንዲሆን እግዚአብሔርን
አምናለሁና።”
• የእግዚአብሄርን መልዕክት ከመልአኩ ሰማ (ቁ.24)
• እግዚአብሄርን አመነ (ቁ.23)
• ለሌሎች የምስራች በመንገር በእምነት ተራመደ (ቁ.22)
ሰው እንዴት እምነት ሊኖረው ይችላል?
ሁሉም ሰው ብዙ ነገሮችንና ብዙ ሰዎችን እናምናለን። ለምሳሌ ያህል፡-
• መድኀኒት ክኒን የምንወስደው ከበሽታችን ያድነናል ብለን ‘ስለምናምን’ ነው።
11