Page 11 - Descipleship 101
P. 11
የጴጥሮስን በውሃ ላይ መራመድ እንደ ምሳሌ እንውሰድና
ማቴ.14፡22-29 እንመልከት፦ ጌታ ኢየሱስ ጴጥሮስን በውሃ ላይ ተራመድ አለው። ጴጥሮስ ጌታ ኢየሱስ የእ/ር ልጅ መሆኑን ያውቅ ነበር። በተጨማሪም ቢሰጥም እንኳ ክርስቶሰ ሊያወጣው እንደሚችል ያምን ስለነበር ከታንኳ ወርዶ በውሃ ላይ መራመድ ጀመረ።
ተጨማሪ ምሳሌዎች እንመልከት:- 1. አብርሃም ዘፍ. 15፡1-6
“
ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም
መጣ፥ እንዲህ ሲል። አብራም ሆይ፥ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤
ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው። አብራምም። አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥
ምንን ትሰጠኛለህ? እኔም ያለ ልጅ እሄዳለሁ፤ የቤቴም መጋቢ
የደማስቆ ሰው ይህ ኤሊዔዘር ነው አለ። አብራምም። ለእኔ ዘር
አልሰጠኸኝም፤ እነሆም፥ በቤቴ የተወለደ ሰው ይወርሰኛል
አለ። እነሆም፥ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት። ይህ
አይወርስህም፤ ነገር ግን ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል። ወደ
ሜዳም አወጣውና። ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም
ልትቈጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ቍጠር አለው። ዘርህም እንደዚሁ
ይሆናል አለው። አብራምም በእግዚአብሔር አመነ፥ ጽድቅም ሆኖ
ተቈጠረለት።”
• አብርሃም የእግዚአብሄርን ቃል ሰማ (ቁ. 4)
• እግዚአብሄር የገባለትን ተስፋ እንደሚፈጽም እርግጠኛ ነበር
(ቁ. 5)
• በእግዚአብሄር አመነ (ቁ.6)
10