Page 13 - Descipleship 101
P. 13
• በአውቶቡስ ላይ ተሳፍረን ወደ አንድ ስፍራ የምንሄደው የአውቶብስ ሹፌሩ እኛ ወደምንፈልገው መንገድ ይወስደናል ብለን ‘በማመን’ ነው።
ነገር ግን ለመዳን የሚያስፈልገን እምነት የዚህ አይነቱ እምነት አይደለም። ታዲያ የሚያድነውን እምነት እንዴት እናገኛለን? በአዲስ ኪዳን ትምህርት ውስጥ የተለያየ የእምነት ደረጃ ያላቸው ሰዎች ተጠቅሰዋል።
• የስምዖን ጴጥሮስ ትንሽ እምነት (ማቴ. 14፡31)
• የሮማዊው አለቃ ታላቅ እምነትና (ማቴ.8:10)
• የአብርሃም ጠንካራ እምነት (ሮሜ. 4፡20)
ምናልባት ስለ አብርሃም የጠነከረ እምነት ስናስብ እንደ አብርሃም ያለ የጠነከረ እምነት እንዲኖረን እንመኝ ይሆናል። ከሁሉ ይልቅ በጣም አስፈላጊው ነገር እምነታችንን የምናሳርፍበት ቦታ ነው። በማይረባ መድኀኒት ታላቅ እምነት ከሚኖረን ይልቅ በጥሩ መድኅኒት ትንሽ እምነት ቢኖረን ይመረጣል።
የእምነታችን መሰረት በክርስቶሰ በማመን መዳናችን ነው (ሐዋ.20፡21፤ ቆላ. 1፡4)። ኖኅና ቤተሰቡ የዳኑት በኖኅ እምነት ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ሰው በራሱ ውሳኔ በመርከቧ ውስጥ በመገኘቱ ነው። ኖኅ ወደ መርከቡ አምኖ የገባው በእግዚአብሄር ስለታዘዘ ነው።
12