Page 9 - Descipleship 101
P. 9

እጽፍላችኋለሁ። አባቶች ሆይ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። አባቶች ሆይ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጎበዞች ሆይ ብርቱዎች ስለሆናችሁ የእግዚአብሄርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውንም ስላሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ።” 1ዮሐ.2፡12-14
ይህን መጽሀፍ ስታነብ እያንዳንዱን ጥቅስ አንብብና መረዳትን እንዲሰጥህ እግዚአብሄርን በጸሎት ጠይቀው። እምነት የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ በብዙ ስፍራ ተጽፎ እናገኘዋለን።
• በክርስቶስ በማመን ሃጢያታችን ተወግዷል (ሮሜ.3፡25)
• እምነት ካለን እግዚአብሄር እንደ ጻድቅ ይቆጥረናል. (ሮሜ.
4፡5)
• በእግዚአብሄር ጸጋ በእምነት ድነናል (ኤፌ.2፡8)
• ያለ እምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አንችልም (ዕብ. 11፡6)
እነዚህ ከብዙ በጥቂቱ ስለ እምነት የሚናገሩ ጥቅሶች ናቸው። በተለይም በዕብራውያን 11፡6 ሁላችንም እምነት ሊኖረን እንደሚገባ ያለ እምነትም እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት እንደማንችል ያስተምረናል። እምነት ለመዳን ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ፤ አስፈላጊነቱንም በትክክል ልንረዳ ያስፈልጋል። ያ ብቻ ሳይሆን እንዴት እምነትን ማግኘት እንደምንችል መማር አለብን።
8


























































































   7   8   9   10   11