Page 87 - DINQ MAGAZINE NOVEMBER 2020 EDITION
P. 87

ክገጽ  16  የዞር
                                                                 እንዳያስቸግሩኝ  የመታኋቸው  ነው፤  እንድገድላቸው  ፈቃድ  አላገኘሁም"
                                                                 በማለት መናገሩንም ጋዜጣው በትናንት ዕትሙ አስነብቧል።


                                                                 ታካሂሮ በግድያዎቹ ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖም ከተገኘ በጃፓን ህግ መሰረት
                                                                 የስቅላት ቅጣት ይጠብቀዋል። የፍርድ ሂደቱ የመላ ጃፓናውያንን ቀልብ ሰቅዞ
                                                                 የያዘ ሲሆን በትናንትናው እለትም 600 የሚሆኑ ሰዎች ፍርድ ቤት ለመግባትና
                                                                 ለመከታተል ተሰልፈው መታየታቸውም ተዘግቧል።

                                                                 አቃቤ  ህግ  ባቀረበው  ክስ  መሰረት  ታካሂሮ  የትዊተር  ገፁንም  የከፈተው
                                                                 ራሳቸውን ማጥፋት የሚፈልጉ ሴቶችን በቀላሉ ለማግኘትም ነበር። ሴቶቹም
                                                                 ቀላል ኢላማ ሆነውለታል።

                                                                 ከሟቾቹ መካከል ስምንቱ ሴቶች ሲሆኑ ሶስቱ ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ
                                                                 ናቸው። የአስራ አምስት አመት ታዳጊና አራቱ ደግሞ በሃያዎቹ የእድሜ ክልል
                                                                 የሚገኙ ናቸው።


                                                                 ታካሂሮ  የገደለው  ብቸኛው  ወንድም  20  አመቱ  ሲሆን  የጠፋችበት  የሴት
                                                                 ጓደኛው የት አደረስካት በሚል እሰጣገባ በተፈጠረ ግጭት ነው ተብሏል።
                                                                 የ27 አመቱ ታካሂሮ እነዚህን ሴቶች በቀላሉ ራሳቸውን የሚያጠፉበት መንገድ
                                                                 እንዳለውና ራሱንም አብሯቸው እንደሚያጠፋ ገልጾላቸዋል።

                                                                 በትዊተር ገፁም ላይ "በከፍተኛ ህመም ላይ ያሉ ሰዎችን መርዳት እፈልጋለሁ።
                                                                 በማንኛውም  ሰዓት  በመልእክት  ሳጥኔ  በቀጥታ  መልእክታችሁን  አድርሱኝ"
                                                                 ይላል።
                                                                                          ከአድማሰ ሬድዮ የተገኙ ዜናዎች ናቸው




           DINQ MEGAZINE       November 2020                                           STAY SAFE                                                                                    87
   82   83   84   85   86   87   88   89   90   91   92