Page 3 - አብን
P. 3

አብን





                መቅድም


             ለበርካታ  አስርት  ዓመታት  በተግባር  ላይ  የዋለው  የጥላቻና
             የፍረጃ ፖለቲካ አገራችንን ለማያባራ ምስቅልቅል እንደዳረጋት
             ይታወቃል፡፡  በተለይ  በአማራ  ሕዝብ  ላይ  መጠነሰፊ  የሆኑ
             የሕይወትና  የንብረት  ውድመቶችን  አስከተሎና  በማህበራዊ
             ስነልቦናው ላይም ከፍተኛ ጫና ፈጥሮ ይገኛል፡፡


             በአማራው  ላይ  ሲፈጸሙ  የቆዩት  ጥቃቶች  በዘር  ማጥፋት
             ደረጃ  እየተገለጡ  መምጣታቸውና  አጠቃላይ  የህልዉና  አደጋ
             የጋረጡ መሆኑን በማመን፤


             ጥቃቶቹ  የተደራጁ፤  የተቀናጁና  የጥላቻ  ትርክት  መሰረት
             ያላቸው  መሆኑን  በመረዳት፤  በህገመንግስትና  በሕግጋት፤

             በፖሊሲዎችና  ፕሮግራሞች  እንዲሁም  በመዋቅሮች  የተደገፉ
             መሆናቸውን በመረዳት፤


             ሰፊው  የሀገራዊና  መንግስታዊ  የማደራጃ  መርህ  አማራ
             ጠልነት  ተላብሶ  መቆየቱና  የተቃውሞው  ጎራም  በአመዛኙ
             ተቀራራቢ  ብያኔ  መስጠቱ  እንዲሁም  በጽንፈኛ  ሀይሎች
             የገንዘብና  የጠመንጃ  ብልጫ  የተወሰደበት  መሆኑ  የአማራ
             ህዝብ  የተደራጀ  ትግል  ምእራፍ  ውስጥ  እንዲገባ  ምክንያት
             ሆነዋል፡፡


             “የአንድነቱ  ጎራ”  በራሱ  የጠራ  አቋም  የሌለውና  የተለሳለሰ፤
             እርስበርሱ  የሚሻኮት፤  የሚጠላለፍና  ለሰርጎ  ገቦች  የተጋለጠ

                1   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   1   2   3   4   5   6   7   8