Page 7 - አብን
P. 7

አብን


             የሚሉ ምንዝር ፍረጃዎች ተለጥፈውበት ለዘር ማጽዳትና ለዘር

             ማጥፋት  ወንጀሎች  ሰለባ  ሆኖ  ይገኛል፡፡  በዚህ  አግባብ
             የተፈጸሙት  ጥቃቶችና  ጥፋቶች  ምድብና  ዝርዝር  በውል
             ሳይታወቅ  በጥቅሉ  ድምጽ  አልባ  ለሆኑ  ተደጋጋሚ  የዘር
             ፍጅቶች ተጋልጦ ቆይቷል፡፡


             በሂደት  በተለያዩ  አካባቢዎች  የሚኖሩ  የአማራ  ልጆች
             የበደሎቹን መነሻና አንድምታ በአግባቡ ለመረዳት፤ ለማጋለጥና
             ለመከላከል  ያስችላሉ  ያሏቸውን  የትግል  ስልቶች  በመጠቀም
             እንቅስቃሴዎችን  ለማድረግ  ሞክረዋል፡፡  ትግሉ  የተለያዩ
             ቅርጾችን  በመያዝና  ስልቶችን  በመከተል  ለረጅም  ጊዜ  የቀጠለ
             ቢሆንም ይህ ነው የሚባል ስኬት ማስመዘግብ አልቻለም ነበር፡

             ፡  መንግስት  በቀጥታና  በእጅ  አዙር  በማንአለብኝነትና
             በአምባገነንነት የሚፈጽማቸውን ግለሰባዊና ማህበራዊ ጥቃቶች
             ለማጠናከር        ኢሞራላዊ፤         ኢሰብዓዊና         ኢ-ሕገመንግስታዊ
             እንዲሁም  ከአለማቀፍ  ህግጋት  ጋር  የሚቃረኑ  አፋኝ
             አዋጆችንና  ደንቦችን  በማውጣት  ርቃን  የወጡ  የዘር
             ጥቃቶችንና         የሰብአዊ       መብት       ጥሰቶችን        የሚፈጽሙ

             መዋቅሮችን ዘርግቶ ይፋ ስምሪት ወስዶ ቆይቷል፡፡

             በሌላ  በኩል  በሁሉም  አቅጣጫና  ዘርፍ  በተበታተነ  መልኩ

             ሲተገበር  የቆየው  የተቃውሞና  የመከላከል  ትግል  ከፍተኛ
             አጣብቂኝ       ዉስጥ       እየወደቀ       ባለበት      ወቅት       የአማራ
             ብሄርተኝነትን  የማደራጃ  መርህ  ማድረግ  ያስፈልጋል  የሚል
             ፖለቲካዊ  አስተሳሰብ  የታሪክና  የዘመንን  ጥሪ  አዳምጦ
             ወደመድረክ  ብቅ  አለ፡፡  የአማራ  ሕዝብ  ትግል  በግንባር
             ቀደምነት  ሊመራ  የሚገባው  በቅርብ  ተፈጥሯዊ  ባለቤቱ

                5   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   2   3   4   5   6   7   8   9   10   11   12