Page 9 - አብን
P. 9

አብን


             ይታወቃል፡፡  በረጅሙ  የሰቆቃ  ዘመን  ውስጥ  ጥቃት

             የፈጸሙበት፣ ከጎኑ ያልቆሙና ብሶቱ እንኳ በቅጡ እንዳይነገር
             የተባበሩ፣  ለግብዓት  ሲፈልጉት  የሚጠሩት  ነገር  ግን
             ሲጠራቸው  የማይሰሙ  አካላት  “አማራ  ከተደራጀ  ሀገር
             ይፈርሳል”  እና  ”የአማራዉ  መደራጀት  ለመጠቃቱ  ምክንያት
             ነው”  የሚሉ  ውዥንብሮችን  በመንዛት  ለማስተጓጎል  ሲሞክሩ
             አስተውለናል፡፡  የአማራ  ህዝብ  መደራጀት  ከመጀመሩ  በፊት
             በርካታ  ዘር  ተኮር  ጥቃቶች  እንደተፈጸሙበት  እየታወቀ
             መደራጀቱን  ለጥቃቶቹ  ምክንያት  አድርጎ  ማቅረብ  ግብዝነት

             ነው፡፡

             ማንነትን  መሰረት  ያደረገ  ፖለቲካ  የሀገራችን  የመንግስት

             ማደራጃና  የሉዓላዊ  ስልጣን  ባለቤትነት  መሰረት  ስለመሆኑ
             ሕገመንግስታዊ  ድጋፍ  እንደተቸረው  ይታወቃል፡፡  የማንነት
             አደረጃጀት        የኢትዮጵያ         ፓርላማ        የከፍተኛው         ምክር
             ቤት/የፌዴሬሽን  ምክር  ቤት/  የሚዋቀርበት  መርህ  ነው፡፡
             የሀገሪቱን  ሕገመንግስት  ለማሻሻል  የፌዴሬሽን  ምክርቤቱን
             ይሁንታ ማግኘት እንደሚገባ በሕገመንግስቱ አንቀጽ 105/1/ለ/

             ላይ  ተደንግጓል፡፡  ምክር  ቤቱ  ሕገመንግስቱ  ውስጥ  የተደነገጉ
             በርካታና  ወሳኝ  ስልጣኖች  እንዳሉትም  ይታወቃል፡፡  በተግባር
             ከሚታየው  የፖለቲካ  ተዋስኦ  በተጨማሪ  በጽንሰሀሳብና
             በሕገመንግስቱ ድንጋጌዎች አግባብ ሲታይ በማንነት መደራጀት
             በሀገራችን  ማህበራዊ  ህግና  ፖለቲካ  ውስጥ  ገዥ  መርህ
             መሆኑን  እንረዳለን፡፡  ስለሆነም  የአማራ  ህዝብ  ማንነቱን
             መሰረት  አድርጎ  በጽኑ  ለመደራጀት  የሚያደርገው  እንቅስቃሴ
             አሁን ባለው መዋቅር እና ስርዓት መሰረት አማራጭ የሌለው

             ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ማንነትን መሰረት ባደረገ የፖለቲካ ድርድር
                7   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   4   5   6   7   8   9   10   11   12   13   14