Page 11 - አብን
P. 11
አብን
የአማራ ሚኒሻ ሀገርንና ህዝብን መታደግ የቻለ ታሪካዊ
ሀላፊነታቸውን በብቃት ተወጥተዋል፡፡ የአማራ ህዝብና በስሙ
የተደራጁ የፖለቲካ ሀይሎችም በአንድነት ከሀገራቸው ጎን
ተሰልፈው አለኝታነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ከዚህ የምንረዳው
የአማራ መደራጀት ለሀገር አንድነትና ቀጣይነት አስጊ ሳይሆን
አስፈላጊ መሆኑን ነው!
ከላይ የአማራ ህዝብ መደራጀት እስካሁን ድረስ በታዩ
ተሞክሮዎችና ተፈትሸው በተረጋገጡ መርሆዎች ሙሉ
በሙሉ የሚደገፍ ጉዳይ እንደሆነ ለማየት ይቻላል፡፡ በዚህ
ጭብጥ ዙሪያ በርካታ የሆኑ ዝርዝር የመከራከሪያ ነጥቦችን
በማንሳት የአማራን ህዝብ የፖለቲካና የአደረጃጀት ሂደት
ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንችላለን፡፡
የሀገራችን የፖለቲካ ባህል ያፈራቸው አደረጃጀቶች ኢትዮጵያን
ወደፊት ማራመድም ይሁን ራሳቸው ስንዝር መጓዝ
የተሳናቸው በመሆኑ የኋልዮሽ ጉዞው ቀጥሎ ይገኛል፡፡
መንግስትን ጨምሮ በተለያዩ ጎራዎች የተሰለፉ አካላት
በሀገራችን ውስጥ ጥላቻ የተላበሰ ፖለቲካ ባህል እንዲዳብር
የየራሳቸው ድርሻ አላቸው፡፡
በአንድ በኩል በሀገራችን ታሪክ ዙሪያ የሚታየው ጥራዝ ነጠቅ
ንባብ ያስከተለው ውስብስብ ችግር የጋራ ማህበራዊ ምልከታ
እንዳይኖር ችግር ከመፍጠሩም በላይ ሁሉንም ነገር ከሀገራዊ
ማንነትና ፍላጎት በተቃርኖ የመቆም አባዜ የተጠናወታቸው
አካላትን አላማ ለማሳካት በጥላቻ ዙሪያ ሀይል ለማሰባሰብና
ለመደራጀት ምቹ እድል አድርገው ሲጠቀሙበት ቆይተዋል፡፡
9 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !