Page 14 - አብን
P. 14
አብን
በሀገራችን በ1960ዎቹ ውስጥ የተጀመሩ ጥራዝ ነጠቅ
የመደብና የብሄር ፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የተሳተፉ
ወገኖች ተከትሎ ለመጣው ሀገራዊ ምስቅልቅል ድርሻ
እንዳላቸው አይዘነጋም፡፡ በተለይ በርካታ የአማራ ልጆች
እንደዋዛ የተሰለፉባቸው እንቅስቃሴዎች ለተፈጸሙት የዘር
ፍጅቶች ምክንያት እንደሆኑ ስለሚታሰብ ከወገኖቻቸው በጎ
ትውስታ ውጭ ለመሆን ተዳርገዋል፡፡
ከላይ በተመላከቱት ሀሳቦች መነሻነት ያለፈውን ታሪክ በአግባቡ
በማጥናት፣ አሁንና ወደፊት የሚያስፈልገንን በመለየት፣
ግባችን ላይ ለመድረስ የሚያስችል የሀሳብ ጥራት በመያዝና
አስቻይ የሆነ አደረጃጀት በመፍጠር የአማራን ህዝብና
ኢትዮጵያን ለመታገድ የምናደርገውን መንታ ትግል አጠናክረን
እንቀጥላለን፡፡
ምንም እንኳን የአማራ ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎችና
የሀገራችን ችግሮች በምርጫ ብቻ እንደማይፈቱ የምንገነዘብ
ቢሆንም በተራዘመ ጊዜ ውስጥ የተጠናከረ ትግል በማድረግ
መፈታት የሚችሉትን ጥያቄዎች ለመድረክ በማብቃት እልባት
እንዲያገኙ የሚያስችል መነሻ አማራዊ የፖለቲካ ሀይል
መፍጠር መሰረታዊ ትኩረት ተደርጎ ሊከናወን እንደሚገባ
መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ምርጫ መሰረታዊ መብት ነው፡፡ ምርጫ
የዴሞክራሲያዊ ሂደትና ስርአት አይነተኛ መገለጫ ነው፡፡
ምርጫ የህዝብ ሉአላዊነት መገለጫም ነው፡፡ ሆኖም ምርጫ
የአስቻይ ሁኔታዎችን መኖር የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡ የተሟሉ
መደላድሎች የሌሉበት ምርጫ የይስሙላ ሂደት ሲሆን
ተጨማሪ ችግሮንና ቀውሶችንም ሊያስከትል የሚችል ነው፡፡
12 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !