Page 16 - አብን
P. 16
አብን
በዘላቂነት ነጻ መዉጣት እንዳለባትና መሰረታዊ የፖሊሲና
ህግጋት እንዲሁም የመዋቅር ክለሳ መደረግ እንዳለበት ጽኑ
እምነት ቢኖረውም ጊዜያዊ በሆነ የጥሬ ስልጣን ግብግብ
የታገቱ አካላት ፍላጎት በተቃራኒዉ መሆኑና ከዜሮ ድምር
ውጭ ፖለቲካዊ አማካይ የሚባል እሳቤ የሌላቸው ስብስቦች
ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊሳካ
እንደማይችል በመገንዘብ በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍ ወስኖ
እንቅስቃሴ ውስጥ ገብቷል፡፡ አብን ወደምርጫ ለመግባት
ሲወስን በተቻለ መጠን ሂደቱንና ውጤቱን ወደፊት በሀገራችን
ለሚኖረው የተጠናከረና የተቀናጀ የፖለቲካ ትግል መነሻ
የሚሆን የበጎ ሀይሎች ትብብር ለመፍጠር በመልካም
አጋጣሚነት ወስዶ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ንቅናቄያችን አብን
በመረጃና እውቀት ላይ የተመሰረተ የሀይል አሰላለፍ ትንተና
በመስራትና ተጓዳኝ ግምገማዎችን በማድረግ በአንኳር
ስትራቴጂክ ግቦች ዙሪያ ተቀራራቢ ምልከታ ካላቸው የፖለቲካ
ፓርቲዎች ጋር በትብብር ለመስራት እቅድ አውጥቶ ተግባራዊ
ማድረግ ጀምሯል፡፡ በዚህ ረገድ ከበርካታ ፓርቲዎች ጋር
አብሮ መስራት የሚያስችል ስምምነት ላይ ለመድረስ
ምክክሮችን በማድረግ ላይ ሲሆን በቅርቡ ከባልደራስ
ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጋር ይፋ የፖለቲካዊ ትብብር
ስምምነት ፈጽሟል፡፡ ይህ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠል
እንዳለበት በማመን በተለይም ሀገራችንን ካለችበት ምስቅልቅል
ለማውጣት ይቻል ዘንድ በጥቃቅን ልዩነቶች ላይ ያልተገባ
ትኩረት ከመስጠትና በተናጠል ከመቆም ይልቅ በትብብር
የተቀናጀ ትግል ማድረግ እንደሚገባ በመገንዘብ ድርጅታዊ
ቅርብ አዳሪነትንና ዘላቂ ስትራቴጂክ ግብን በመናኛ ታክቲክ
14 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !