Page 13 - አብን
P. 13

አብን


             የተጠመዱ  አካላት  የፖለቲካ  ሜዳውን  ሞልተውት  እንደቆዩ

             የምንገነዘበው ሀቅ ነው፡፡

             በተጓዳኝ በአፋኝ፣ ዘረኛና ገዳይ ስርአቶች በሚያደርሱት ጥቃት

             ጫና  እየተፈጠረባቸውና  አባል የሆኑባቸው ድርጅቶች አስቻይ
             ካለመሆን  አልፈው  የሴራ  መረብና  ተጋላጭ  ስላደረጓቸው
             በርካታ  ወንድሞችና  እህቶቻችን  በየጊዜው  መስዋእትነት
             እየከፈሉ  ነገር  ግን  አላማቸውን  ሳያሳኩ  የቀሩበትን  ረጅም
             ዘመን      ማስታወስ        ያስቆጫል፡፡        አሰላለፉ      ሁሉ      ሃቀኛ
             እየመሰላቸው  በቅንነት  ሲታገሉ  በህይወታቸው  ጭምር  ዋጋ
             ለከፈሉት ወገኖቻችን ክብር መስጠት ይገባል፡፡ ሆኖም ከአሁን
             በኋላ በተላላነት የምንከፍለው ተጨማሪ ዋጋ መኖር የለበትም፡

             ፡

             በሀገራችን  የመደብና  የብሄር  ትግሎች  ውስጥ  በደጋፊነት፣

             በአባልነት፣  በመሪነት  እንዲሁም  ምሁራዊ  ዘር  በማቀበል
             የተሳተፉ  የአማራ  ልጆች  እንደዋዛ  ወድቀዉ  የቀሩበትን፣
             ከአውድ  ውጭ  ለሆነ  ማጣቀሻ  ግብዓትነት  ውጭ  ውለታቸው
             የተዘነጋበት  ሚስጥር  መመርመር  አለበት፡፡  አሁን  ያለው
             አብዛኛው  አማራዊ  ትውልድ  በፖለቲካ  አሰላለፍ  እና  በሰዎች
             ረድፍ ውስጥ መገኘት የተለያዩ እንደሆኑ ለመገንዘብ ችሏል፡፡


             የአንድ  ትግል  ስትራቴጂክ  መዳረሻ  ራሱ  “ትግል”  ሊሆን
             አይገባም!  መዳረሻውን  በቅጡ  ያልተለመ  ራዕዩን  ማሳካት

             አይችልም፡፡ በህዝብና በሀገር ላይ ሊካካስ የማይችል ውድመት
             ከሚያስከትሉ እንቅስቃሴዎች መታቀብ ያስፈልጋል፡፡



               11   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   8   9   10   11   12   13   14   15   16   17   18