Page 17 - አብን
P. 17
አብን
ከማስተጓጎል የተላቀቀ ስልት መቀየስ እንደሚገባ ለማሳየት
በተግባር ዓርአያ ሆኗል፡፡ አብን ለረጅም ዘመን ከቆየዉና
አሁንም ነባራዊ ሆኖ ከቀጠለው በእኔ ብቻ የታጠረ የዜሮ
ድምር የፖለቲካ ዘይቤ በጽኑ በመፋታት የጋራ አሸናፊነትና
የጋራ ተጠቀሚነት ባህል እንዲጎለብት ያለውን ፍላጎት
ለማረጋገጥ ተምሳሌት ሆኖ ቀርቧል፡፡
በዚህ ታሳቢነት የአማራ ህዝብ ሀቀኛ ወኪሎች በክልላዊና
በፌዴራል የመንግስት መዋቅሮች መወከልና የስልጣን ባለቤት
መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ በአማራ ህዝብ ትግል ሂደት የአማራ
ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን) የህዝባችን የነጻነት ትግል ቀጥተኛ
ውጤት ሲሆን በቀጣይም ወሳኝ ድምጽና ወኪል ሆኖ
እንደሚዘልቅ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት ድርጅት መሆኑ
አይዘነጋም፡፡ የህዝባችንን መሰረታዊ ጥያቄዎች በጥናት
በመለየት ፖሊሲዎችን ቀርጾና ስትራቴጂዎችን ነድፎ ሰፊ
የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ የሚገኝ አይተኛ የህዝባችን
አለኝታና ወካይ ድርጅት ለመሆን በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል፡
፡ ንቅናቄያችን ፕግራምና ደንብ ቀርጾ በሀገራዊ ፓርቲነት
ተመዝግቦ በቀጣዩ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ለመሳተፍ
በሁሉም ረገድ በቂ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡
ከምርጫ አዋጅ ደንብና መመሪያዎች በተጨማሪ የራሱን
እንቅስቃሴዎችና አሰራር በተመለከተ ውስጣዊ ደንቦችንና
መመሪያዎችን በማውጣት ትግሉ ትክክለኛውን መስመር
ተከትሎ እውን እንዲሆን በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን
ቆይቷል፡፡
15 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !