Page 22 - አብን
P. 22
አብን
በገዥው ፓርቲ በኩል እንዲሟሉም ፍላጎቱ እንደሌለ
ለመገንዘብ ችለናል፡፡
የብልፅግና ፓርቲ ሌላው ዓይነተኛ ድክመት የኢትዮጵያዊነትን
እሴት በጭንብልነት መጠቀም ሲሆን በተግባር ላይ የዋለው
አካሄድ ግን ልክ እንደ ህወሓት በነገድ ፖለቲካ ላይ የተገነባ
የመሆኑ ሃቅ ነው፡፡ ሕገመንግስቱ እንዲለወጥ
የማይፈልገውም፤ ይኸው ከህወሃት ለወረሰው የዘውግ ፖለቲካ
የኦሮሚያ ብልፅግና ታማኝ ሆኖ በመቀጠሉ ነው፡፡
1.2. ህወሓትን በአካል መዋጋት እና የህወሓትን አስተምህሮ
በታማኝነት ማስቀጠል
በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ህወሓት በጫረው
ጦርነት ሳቢያ በተከፈተው ውጊያ የህወሓት ወታደራዊ ሃይል
ከጥቅም ውጭ እንዲሆን ቢደረግም፣ የኦሮሞ ብልጽግና
የህወሓትን አስተምህሮ በታማኝነት ሲያስቀጥል እየተስተዋለ
ነው፡፡
ህወሓት እና ኦነግ የቀመሩትን ሕገመንግስት ለመቀየር
እንደማይፈልግ በገሃድ አስታውቋል፡፡ የቋንቋ ፌደራሊዝሙ
መለወጡን እንደማይፈልግ ብቻ ሳይሆን እንዲለወጥ
የሚፈለጉትን አምርሮ እንደሚታገል ገልጿል፡፡ በሃሰት የታሪክ
ትርክት ላይ የተገነባውን የጨቋኝ-ተጨቋኝ ብሔረሰቦች
አመለካከት የሙጥኝ ብሎ ይዟል፡፡ ከዚያም ባሻገር ዋጭ
ሰልቃጭ የሆነውን እና ያልተገራ ፍላጎቱን ለማሳካት በአገሪቱ
በአራቱም ማዕዘናት ሁከት እና ብጥብጦችን አንዲሁም የዘር
ማጥፋት ወንጀሎችን ከጀርባ ሆኖ ከመዘወር ከፍ ብሎ በፊት
20 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !