Page 25 - አብን
P. 25
አብን
ማህበረሰብ ድርጅቶች ነፃነት፣ በዲሞክራሲያዊ ተቋሞች
ምስረታና ብቃት እንዲሁም በአፈፃፀማቸው ውጤታማነት
ወዘተ….ሃገራችን የምትገኝበት ደረጃ ከመጨረሻዎቹ ተርታ
እንደሆነ አመላክቷል፡፡ ህዝቡ መልካም አስተዳደር ለመቀዳጀት
ዘመናትን ያስቆጠረ፣ በመስዋዕትነት የታጀበ ትግል ሲያካሂድ
ቢኖርም፣ የሃገሪቱ የፖለቲካ ልሂቃን የስልጣን ጥማታቸውን
ለሀገር ጥቅም ለማስገዛት ባለመቻላቸው እና ባለመፍቀዳቸው፣
በተፈጥሮ ፀጋ የታደላት አገር በአስተዳደር በደል እድገቷ
እየተገታ ሳታጣ ያጣች ተመፅዋችና ሀገር ለመሆን ተገዳለች፡፡
1.7. የሲቪል ሰርቪሱ በተረኝነት መታመስና ተቋማዊ
ሙስና
የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሞ ክንፍ ህወሀት ዘርግቶ ከሄደው
የተቋማዊ እና መንግስታዊ ሙስና እራሱን ለማጽዳት
ያለመፈለጉ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ስልጣንን መከታ በማድረግ
የሚከናወንን ተቋማዊ ሙስና በተረኝነት መንፈስ አጠናክሮ
በመቀጠል ላይ ስለመሆኑ ብዙ ማስረጃዎች ማቅረብ ይቻላል፡፡
የመንግስት ስልጣንን ለሃገር ሳይሆን ለነገድ ጥቅም የማዋል
የሃገር ስልጣን በመማረክ የሚፈፀም ተቋማዊ ሙሰኝነት
(State capture ) ነው፡፡ ይህ ህወሓት ቀደም ሲል በነፃ ገበያ
ሞዴል በኋላም በልማታዊ መንግስት ሸፋን ይከተለው የነበረው
መመዘኛ በከፊልም ከህወሓት ጋር ንክኪ የነበራቸውን
በአብዛኛው የዘውግ ኢኮኖሚ ተዋንያኖችን የሚያበልፅግ ነበር፡፡
የህወሓት የልማት ቀመር በእጅጉ የተዛባ እና ከሃገራዊ እና
ማህበራዊ ፍትህ ጋር ያልተገናዘበ የሃገር ሃብት ክፍፍልን
ያስከተለ ነበር፡፡
23 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !