Page 23 - አብን
P. 23

አብን


             ለፊት  እየተገለጠ  መምጣቱ  ሌላውን  ብንተወው  በቅርቡ

             በአጣየና  ማጀቴ፣  እንዲሁም  በምእራብ  ወለጋ  በስፋት
             የተፈጸመውን  የዘር  ማጥፋት  ወንጀል  በቂ  ማረጋገጫ  ነው፡፡
             ይህንንም        ከሞት        የተረፉ        ወገኖቻችን         ምስክርነት
             የሚያረጋግጥልንን ያህል አጣየን አስመልክቶ በችኩል የወጣው
             የኦሮምያ  ክልላዊ  መንግስት  መግለጫና  ነውረኛ  የፓርላማ
             ውሎ  ንግግሮች  ጭምር  በህዝባችን  ላይ  የደረሰው  ጥፋት
             መንግስታዊነትን የተላበሰ ለመሆኑ በቂ ማስረጃወች ናቸው፡፡


             1.3.   የሀገሪቱን ሰላም እና ፀጥታ ማስከበር አለመቻል

             ብልጽግና  ፓርቲ  እንደ  ገዥ  ፓርቲነቱ  የሃገሪቱን  የውስጥ
             ሰላምና  ፀጥታ  ማስከበር  ሲገባው፣  ባለፉት  ሶስት  አመታት
             ከዚህ  ቀደም  ታይቶ  በማይታወቅ  ሁኔታ  በሃገሪቱ  ሁሉም
             ማዕዘናት  ሕዝቡ  በፀጥታ  እጦት  እየታመሰ  ይገኛል፡፡  የነገድ
             ፖለቲካውን  ለማራመድ  በሚደረግ  ጥረት  በሃገር  ውስጥ

             ተፈናቃዮች  ብዛት  ሃገራችን  ከሶሪያና  ከየመን  በልጣ  በአንደኛ
             ደረጃነት ተመዝግባለች፡፡

             የሰላም  እና  የፀጥታ  ሁኔታው  መደፍረሱ  ሳይበቃ  ሃገራችን
             አስከፊ      የሰብዓዊ       እልቂተና       የዘር     ማጥፋት        ወንጀል
             የሚፈፀምባት  አገር  ሁናለች፡፡  በኢትዮጵያ  ውስጥ  በ2012
             በኦሮሚያ ብዛት ባላቸው አካባቢዎች ማንነትን ማለትም አማራ
             ተኮር  አሰቃቂ  እልቂት  ከመከናወኑም  በላይ፣  ይህ  አይነት

             አስከፊ  የዘር  ማጥፋት  ወንጀል  በ2013  ዓ.ም  ሳያባራ
             እየተፈጸመ  ይገኛል፡፡  የአማራ  ተወላጆች  በኦሮሚያ  ክልል
             በርካታ  ከተሞች  (እንደ  ሻሸመኔ  ወዘተ)  ለህይወት  መጥፋት
             ተዳርገዋል          በከፍተኛ         ደረጃ        ሃብትና         ንብረት

               21   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   18   19   20   21   22   23   24   25   26   27   28