Page 18 - አብን
P. 18

አብን


             የአብንን  ፖለቲካዊ፣  ማህበራዊና  ኢኮኖሚያዊ  ምልከታዎች

             በተመለከተ  መራጩ  ህዝብ  ተገቢዉን  አማራጭ  እንዲገነዘብ
             ለማስቻል  ማኒፌስቶ  ማዘጋጀት  አስፈልጓል፡፡  ይህ  የምርጫ
             ማኒፌስቶ  አብን  በአጭር  ጊዜ  ውስጥ  በኢትዮጵያ  ፖለቲካ
             ውስጥ  በሳልና  ገንቢ  ሚና  በመጫወት  ያገኘውን  ሰፊ  ህዝባዊ
             ድጋፍና  አመኔታ  ወደ  ህዝብ  ድምፅ  በመቀየር  የሚቀዳጀውን
             መንግሥታዊ  ሥልጣን  ለአማራ  ህዝብ  ብሎም  ለመላው
             ኢትዮጵያውያን  ጥቅም  ለማዋል  ቃል  የሚገባበት  የተግባር
             ሰነድ ነው፡፡


             ማኒፌስቶው  በህዝባችን፣  በታሪካችን፣  በባህላችን  ላይ  ያለንን
             መተማመንና  ክብር  የሚያንፀባርቅ  በጥልቅ  ምክክርና  ጥናት
             ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ይሄም በተግባር ሊተረጎምና ሊደረስበት
             የሚችል መርሃ ግብር ነው፡፡

             ማኒፌስቶው  በሶስት  ዋና  ዋና  ክፍሎች  የቀረበ  ሲሆን

             የመጀመሪያው  ክፍል  የነባራዊ  ሁኔታ  ግምገማ  የቀረበበት፣
             ሁለተኛው  ክፍል  ደግሞ  የአብን  አማራጭ  ፖሊሲ  ሃሳቦች
             የቀረቡበት ሲሆን ሶስተኛው ክፍል ማጠቀለያ  ነው፡፡ ክፍሎቹ
             በውስጣቸው የተለያዩ ምዕራፎችን አካተዋል፡፡

             በማኒፌስቶው  የቀረበው  የአብን  አማራጭ  ርዕይ  ንቅናቄያችን

             ሀገር የማስተዳደር ሃላፊነትን ለመሸከምና በአግባቡ ለመወጣት
             ዝግጁነቱን የሚያረጋግጥበት ነው፡፡ አስተዋዩ ህዝባችን አዳዲስ
             አማራጮችን  እንዲመዝንና  በብሩህ  ተስፋ  እንዲነሳ  የሚጋብዝ
             ጥሪ ነው፡፡





               16   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   13   14   15   16   17   18   19   20   21   22   23