Page 21 - አብን
P. 21

አብን


             ህውሃት  ተክሏቸው  የሄዱ  ለአምባገነናዊ  አገዛዝ                   የሚያመቹ

             ህጎችን  የመለወጥና  ተቋሞችን  የማስተካከል  እና  የመለወጥ
             ፍላጎት  እንደሌለው  ግልጽ  አድርጓል፡፡  እንደ  መከላከያ፣
             ደህንነት  እና  ፖሊስ  ያሉ  ተቋሞችን  ዴሞክራሲያዊ  ስርዓቱን
             ስር  ለማስያዝ  እና  ለማጎልበት  ቁልፍ  ሚና  እንዲጫወቱ
             ከማድረግ  ይልቅ  የገዥው  ፓርቲ  ፍላጎት  ማስፈፀሚያ  ሆነው
             ቀጥለዋል፡፡  የሚዲያ  ተቋሞች  በገለልተኛነት  እንዲሰሩ
             ለማድረግ  አልተሞከረም፡፡  የፍትህ  ስርዓቱ  በገዢው  ፓርቲ
             ቁጥጥር  ስር  መሆኑ  በገሃድ  እየታየ  ነው፡፡  የመንግስት

             የአሰራር  ግልጽነት  እና  ተጠያቂነት  የሚባል  ነገር  የለም፡፡
             መንግስት የሚከተለው ፖለቲካ የነገድ ፖለቲካ ከመሆን ሊዘል
             አልቻለም፡፡  ዜጎች  ከሕግ  ውጭ  በሆነ  አሰራር  መብታቸው
             በስፋት  እየተጣሰ  ይገኛል፡፡  በአጠቃላይ  ሲታይ  ከአምባገነናዊ
             አገዛዝ  ወደ  ዲሞክራሲ  በሚደረግ  ሽግግር  መታለፍ  ያለባቸው
             ሁለት  ደረጃዎች  ማለትም  የአምባገነናዊ  አገዛዝን  የመጨቆኛ

             ተቋሞች  እና  አሰራሮችን  የመለወጥ  እና  የማሻሻል  እንዲሁም
             የዲሞክራሲያዊ  ነፃ  እና  ገለልተኛ  የመንግስት  እና  በተለይ
             የሲቪክ ተቋማት ግንባታን በተመለከተ የተከናወነ ነገር የለም፡፡
             ህወሓት  ተክሏቸው  የሄደው  የመጨቆኛ  ተቋሞችና  አሰራሮች
             አሁንም  በሥራ  ላይ  ይገኛሉ፡፡  ዲሞክራሲያዊ  ሂደቱን
             ለማጠናከር፣  ነፃ  እና  ትክክለኛ  ምርጫ  ለማካሄድ  የማያስችሉ
             የክልል  ሚዲያዎች፣  የነገድ  ኢኮኖሚያዊ  እና  የፋይናንስ
             ተቋማት  አሁንም  በነበሩበት  ሁኔታ  ቀጥለዋል፡፡  በአጠቃላይ

             ከሕወሓት  መወገድ  በኋላ  ያለውን  ሁኔታ  ስንገመግም
             ሃገራችንን  ከአገዛዝ  ስርዓት  ወደ  ዲሞክራሲ  ለማሸጋገር
             መሟላት  ያለባቸው  ሁኔታዎች  እንዳልተሟሉ  ብቻ  ሳይሆን


               19   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   16   17   18   19   20   21   22   23   24   25   26