Page 24 - አብን
P. 24

አብን


             እንዲወድምባቸውም  ተደርጓል፡፡  በኦሮሚያ፣  በቤንሻንጉል

             በደቡቡ  አንዳንድ  አካባቢዎች  የተካሄደው  የዘር  ማፅዳት  እና
             ማጥፋት  ወንጀሎች  እንዲሁም  የሕዝብ  ሃብት  ውድመት
             በሃገራችን የቅርብ ጊዜ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው፡፡

             1.4.   የሀገር ሉዓላዊነት መደፈር

             ገዥው የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ የሙጥኝ ብሎ በያዘው የነገድ
             ፖለቲካ ምክንያት በተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች መካከልም ጠብ
             እየተጫረ  ሃገሪቱ  ለሰው  ህይወት  መጥፋትና  ለንብረት
             ውድመት  ተጋልጣለች፡፡  በዚህ  ምክንያት  ውስጣዊ  አንድነቷ

             መላላቱን  የተመለከቱ  የአካባቢው  የሀገራችን  በተለይም  ሱዳን
             የኢትዮጵያን  ሉዓላዊነት  በመድፈር  እና  ድንበር  ጥሳ
             የሃገራችንን  ግዛት  ከመያዟም  በላይ፣  ከፍተኛ  የንብረት
             ውድመት እንዲደርስ አድርጋለች፡፡

             1.5.   የፅንፈኝነት እና የአክራሪነት አደጋ

             በኢትጵያ  ውስጥ  በሚኖሩ  የተለያዩ  ማህበረሰቦች  መካከል

             የነበረው  መተሳሰብና  መደጋገፍ  ህውሓትም  ሆነ  የኦሮሞ
             ብልጽግና        በሚያራምዱት           የነገድ      ፖለቲካ       ምክንያት
             በመሸርሸሩ፣ ሃገራችን የብሔር ጽንፈኛነትን እና የአክራሪነትን
             አደጋ በቁጥጥር ስር ለማዋል አልተቻለም፡፡

             1.6.    የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳዳር እጦት

             ስለ  አፍሪካ  መልካም  አስተዳደር  ሁኔታ  ለመለካትና
             ለመገምገም  የአፍሪካ  ሕብረት  ኮሚሽን  በርከት  ባሉ  የአፍሪካ
             ሀገሮች  ባደረገው  ጥናት  በፖለቲካ  ውክልና፣  ሙስናን

             በመቆጣጠር፣  በኢኮኖሚ  አመራር፣  በሚዲያና  በሲቪል
               22   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   19   20   21   22   23   24   25   26   27   28   29