Page 29 - አብን
P. 29

አብን


             በሃገራችን  ጽንፈኛ  ፖለቲከኞች  የሚያራምዱት  የአዲስ  አበባ

             ኬኛ  ፖለቲካ  ወደ  ዲሞክራሲ  እና  ወደ  መግባባት  ሊያደርስ
             እንደማይችል  ሊገነዘቡት  ይገባል፡፡  ኢትዮጵያ  ነፃ  ነገዶች
             በፈቃደኝነት  በ1983  የመሰረቷት  ሃገር  አይደለችም፡፡  የሺህ
             ዘመናት የሃገረ-መንግስትነት ታሪክ ያላት አገር እንጅ በ19ኛው
             መቶ  ክፍለ  ዘመን  አጼ  ምንሊክ  በሃይል  የገነቧት  አገር
             አይደለችም፡፡  ይህን  የታሪክ  እውነታ  ያልተቀበለ  የፖለቲካ
             አካሄድ  ኢትዮጵያ  ወደ  እርስ  በርስ  ጦርነት  እና  ወደ  ፍጅት
             እንጅ  ወደ  ልማት  እንድታመራ  ሊያደርጋት  እንደማይችል

             መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

             ከዚህ  የታሪክ  እውነታ  ስንነሳ  አዲስ  አበባ  የነዋሪዎቿ  እና
             የመላ  ኢትዮጵያውያን  ዋና  ከተማ  መሆኗን  ከመቀበል  ውጭ
             ሌላ  አማራጭ  ለመከተል  መሞከር  በእጅጉ  አስተዋይነት
             የጎደለው አመለካከት ነው፡፡


             1.9.   የተምታት የሃገር ደህንነት እና የውጭ ፖሊሲ

             የብልጽግና  ፓርቲ  የሚከተለው  የሃገር  ደህንነትና  የውጭ
             ፖሊሲ  የሃገሪቱን  የውስጥ  እና  የውጭ  ስጋቶች  በተገቢው

             ሁኔታ ያገናዘበ አይደለም፡

             የኢትየጵያ  ሀገረ  መንግሥት  በታሪክ  ተንከባለው  በመጡ
             ውርሶች  ምክንያት  በውስጥ  እና  በውጭ  የደህንነት  ስጋቶች
             አሉበት፡፡






               27   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   24   25   26   27   28   29   30   31   32   33   34