Page 33 - አብን
P. 33
አብን
1.9.2.2. የወደብ አልባ ሀገር መሆንና በቀይ ባህር ዙሪያ
ያለው የአረብ እና የሃያላን አገሮች ፉክክር
ያስከተለው ስጋት
ኤርትራ ከኢትዮጵያ ከተገነጠለች በኋላ ኢትዮጵያ የቀይ ባህር
ተዋሳኝነቷን እና የባህር በሯን በማጣቷ ከኢኮኖሚ ተጎጅነት
በተጨማሪ ለሃገራዊ ደህንነት ችግር ተጋልጣ ትገኛለች፡፡
የቀይ ባህር አዋሳኝ የሆኑ የመካከለኛ ምስራቅ የአረብ ሀገራት
በሚከተሉት ፖሊሲ ሳቢያ፣ ኢትዮጵያን በተለይ ምስራቅ
አፍሪካን በአጠቃላይ ለመቆጣጠር የሚያደርጉትን ግፊት
ስትቋቋም የቆየች መሆኗ፣ ከቀጠናው ስትራቲጂካዊነት አንፃር
ሀያላን ሀገራት በመካከላቸው ቀጠናውን ለመቆጣጠር ባላቸው
ፉክክር የሚያደርጉት የእርስበርስ እና የውክልና ፍትጊያ
የሀገራዊ ደህንነት ስጋታችን ነው፡፡ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ
መሆኗ በኢኮኖሚው ረገድ ካሳደረባት ከፍተኛ ጉዳት
በተጨማሪ፣ ለሃገራችን የረዥም ጊዜ የብሄራዊ ደህንነት ስጋት
ሊሆን በቅቷል፡፡
1.9.2.3. የጎረቤት ሀገሮች ስጋት፣ የወደቁ / Failed / እና
በመውደቅ ላይ የሚገኙ / Failing / ጎረቤት
ሀገሮች ስጋት
ሀ/ ሱማሊያ
ሱማሌን ለማረጋጋት በማሰብ ኢትዪጵያ ጦሯን ወደ ሱማሊያ
ካዘመተች በኋላ እንደ አልሸባብ ያሉ የሽብርተኛ ድርጅቶች
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነት ስጋት እንዲሆኑ አድርገዋቸዋል፡፡
31 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !