Page 37 - አብን
P. 37
አብን
ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ ወደብ ሊኖራት ማስፈለጉ
ኤርትራም ከዚህ የወደብ ግንኙነት ተጠቃሚ የሚያደርጋት
መሆኑ የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት ለማጠናር የመጀመሪያ
መነሻ ነው፡፡ ይኸ ሁኔታ እንዳይፈጠር መሰናክል ሲፈጥር
የነበረው ህወሓት በአሁኑ ጊዜ የፖለቲካ ቁመና ስለሌለው፣
በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ሊኖር የሚገባው የኢኮኖሚ
ትስስር ግልፅ እና ይፋ በሆነ መርህ ሊመራ ይገባዋል በውልም
ሊቋጭ ይገባል፡፡
ለዘለቄታው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት ከወደብ
አገልግሎት በእጅጉ የላቀ በሁለቱ ሀገሮች የሚገኝን ተቆራርጦ
ሊቀር የማይችልና የማይገባው የአንድ ሕዝብነት ግንኙነት
በምን መልክ ስርዓት ሊይዝ እንደሚገባው በሁለቱ
መንግሥታት ብቻ ሳይሆን በህዝብ ለህዝብ ደረጃ ውይይት
ሊከፈት ይገባል፡፡
ረ. ኬንያ
የኢትዮጵያና የኬንያ ግንኙነት ኬንያ ነፃነቷን ከተቀናጀችበት
ጊዜ ጀምሮ ዘላቂ ሁኖ የቀጠለ ነው፡፡ ሁለቱም አክራሪ የሱማሌ
ብሔርተኝት እና የጅሃድ እስላማዊ ዋልታረጋጥነት ስጋት
ያለባቸው እንደመሆናቸው መጠን፣ ግንኙነታቸውን
የሚያቀራርብ ቋሚ የጋራ ጉዳይ አላቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ
በሁለቱ ሀገሮች መካከል የተጠናከረ የህዝብ፣ የሸቀጦች እና
አገልግሎቶች ዝውውር አለ፡፡ ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ
በኬንያ የኦሮሞ ማህበረሰቦች በኢትዮጵያ ካሉ ፅንፈኛ የኦሮሞ
ብሄረተኞች ጋር አንዳንድ ግንኙነት እንደላቸው ስለሚዘገብ፣
ኦነግም በዚህ ሂደት ተጠቃሚ ለመሆን በማሰብ ድንበር
35 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !