Page 38 - አብን
P. 38

አብን


             አቋራጭ  እንቅስቃሴዎች  እያደረገ  ስለመሆኑ  መረጃዎች

             እየወጡ  ነው፡፡  ይኸ  ክስተት  ጎላ  ብሎ  የሚወጣው  በኬንያ
             ውስጥ  የሚካሄዱ  ምርጫዎችን  ተከትሎ  ከምርጫ  በኋላ
             ከሚታዩ ጭብጦች ጋር ነው፡፡

             የኢትዮጵያ እና የኬንያ ግኝኙነት ላይ በመካልም ጉርብትና ላይ
             የተመሰረተ  መሆኑ  ለዘለቂታው  ለዚህ  ጤናማ  ግንኙነት

             መሻሻልና መጠንከር ተግቶ መስራት ያስፈልጋል፡፡

             1.9.2.4.  በጎረቤት ሀገሮች የሶስተኛ ወገኖች ጣልቃ ገብነት

             ሱዳን፣  ደቡብ  ሱዳን፣  ሱማሊያ  እና  ጅቡቲን  በተመለከተ
             የአካባቢ  ሀገሮች  መጠቀሚያ  የመሆናቸው  አጋጣሚ  ሰፋ  ያለ
             ነው፡፡  በሱዳን  ውስጥ  ወግ  አጥባቂ  የሆነ  የእስልምና  አቀፍ

             እንቅስቃሴ  በተደጋጋሚ             መከሰት፣  ይህን  አዝማሚያ  ወደ
             ኢትዮጵያ  የማዝመት  አጋጣሚ  ሊያስከትል  የመቻሉ  እድል
             ለኢትዮጵያ  ሃገራዊ  ደህንነት  የስጋት  ምንጭ  ነው፡፡  የደቡብ
             ሱዳንን  መዳከም  ምክንያት  በማድረግ  በጋምቤላ  በኩል  የጎሳ
             ጦርነት  እንዲቀጣጠል  እና  ክፍተቱ  መግቢያ  እንዲሆናቸው
             የሚፈልጉ  በኢትዮጵያ  ታሪካዊ  ጠላትነት  የሚታወቁ  ሀገራት

             በአካባቢው  መግቢያ  እና  መቆናጠጫ  እያፈላለጉ  መሆናቸው
             ለሃገራችን  ፀጥታ  እና  ደህንነት  ስጋት  የሚያጭር  ነው፡፡
             በሱማሌ  ውስጥ  መንግስታዊ  ያልሆኑ  እንደ  አልሸባብ  እና
             አይ.ኤስ.ኤስ ያሉ ሽብርተኛ እና አክራሪ ድርጅቶች ለኢትዮጵያ
             የማይተኙ መሆናቸው፣ በሁሉም  የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገሮች
             ያለው አለመረጋጋት ቁጥሩ በርከት ያለ ስደተኛ ወደ ኢትዪጵያ
             እንዲሰደድ ማድረጉ ሌላ የሃገራችን የብሄራዊ ደህንነት ስጋት
             ነው፡፡

               36   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   33   34   35   36   37   38   39   40   41   42   43