Page 39 - አብን
P. 39

አብን


             1.9.2.5.  የሃያላን መንግስታት ጣልቃ ገብነት


             ህወሓት ራሱ ለከፈተው ጦርነት በተሰጠው ምላሽ ወታደራዊ
             አቋሙ  እንዲፈረካከስ  እና  ፖለቲካዊ  ቁመናውን  እንዲያጣ
             ተደርጓል፡፡  ቀድሞውንም  የደርግን  መንግስት  እንዲጥላላቸው
             በወታደራዊ፣ በፋይናንስ  እንዲሁም በሎጂስቲክስ ሲያግዙ እና
             ሲረዱ  የነበሩ  ምዕራባውያን  ሃገሮች  የህውሓት  ከኢትዮጵያ

             የፖለቲካ መድረክ መወገድ ሊዋጥላቸው አልቻለም፡፡

             በመሆኑም  ዓይን  ባወጣ  ሁኔታ  በኢትዮጵያ  የውስጥ  ጉዳይ
             ጣልቃ  መግባትን  ስራዬ  ብለው  ተያይዘውታል፡፡  ይህ  ሁኔታ
             የሚያስገነዝበን  ነገር  ቢኖር  ግብጽ  እና  ሱዳን  ብቻ  ሳይሆኑ
             ምዕራባውያን  ሃላያን  አገሮችም  ጭምር  ከኢትዮጵያ  የአካባቢ
             ታሪካዊ  ጠላቶች  ጋር  በማበር  ኢትዮጵያ  የተዳከመች  ሆና

             እንድትቀጥል  እና  መብቷንና  ብሔራዊ  ጥቅሟን  የማስከበር
             ችሎታ  እንዳይኖራት  ለማድረግ  ምዕራባውያን  ሃያላን  አገሮች
             ከግብጽ እና ከሱዳን ጎን መሰለፋቸው ፍንትው ብሎ ታይቷል፡፡

             የኢትዮጵያ የሃገር ፀጥታ እና ደህንነት እንዲሁም ተያያዥነት
             ያለው  የሃገሪቱ  የውጭ  ጉዳይ  ፖሊሲ  እነዚህን  ከላይ

             የተዘረዘሩትን የብሄራዊ የስጋት ምንጮች እንዲሁም በየጊዜው
             እየተለዋወጠ  በመምጣት  ላይ  የሚገኘውን  የአለም  አቀፍ  እና
             የሃያላን  ሀገሮች  ኢትየጵያን  በሚመለከት  የሚያራምዱትን
             ፖሊሲ ከግምት ውስጥ በማስገባት መነደፍ ይኖርበታል፡፡







               37   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   34   35   36   37   38   39   40   41   42   43   44