Page 35 - አብን
P. 35

አብን


             የሱዳን  ፖለቲካ  ሱዳን  ነፃ  ከወጣችበት  ጊዜ  ጀምሮ  ከግብፅ

             ፖለቲካዊ ተፅእኖ ተላቆ ስለማያውቅና በዚህ ምክንያት በሱዳን
             ውስጥ  ከግብፅ  ጥቅም  ጋር  የማይሄድ  ፖሊሲ  የሚከተል
             የሱዳን  መንግስትን  ግብጽ  በተደጋሚ  ጊዜ  በወታደራዊ
             መፈንቅለ መንግስት መገልበጧ ይታወቃል፡፡

             ይህን  በሱዳን  ላይ  የተዘረጋ  የግብፅ  የውጭ  ፖሊሲ  ግብፅ

             ከምትከተለው  አባይን  በብቸኝነት  የመጠቀም  ቋሚ  ፖሊሲዋ
             ጋር  ስለሚገናዘብ፣  ሱዳን  ለኢትዮጵያ  የምታሳየው  በመልካም
             ጉርብትና  ላይ  የተመሰረተ  ግንኙነት  ዘላቂ  የሚሆነው
             የኢትዮጵያ  ወታደራዊ ሃይል ተጠናክሮ እስከተገኘ ድረስ  ብቻ
             መሆኑ  በጥቅምት  ወር  2013  በህወሓት  ላይ  የተወሰደውን
             እርምጃ  ተገን  በማድረግ  የፈፀመችው  ወረራ  ቋሚ  ትምህርት
             ሊሰጠን  ይገባል፡፡  ኢትዮጵያ  ወታደራዊ  አቋም  በህወሓት
             እብሪት ምክንያት መዳከሙን ባየችበት ጊዜ ወረራ መፈፀሟ፣

             ሱዳን  የኢትዮጵያ  ቋሚ  ስጋት  እንደምትሆን  የሚያስገነዝብን
             ሃቅ ነው፡፡

             መ. ጅቡቲ
             የጅቡቲ  እና  የኢትዮጵያ  ግንኙነት  ረዥም  ዘመንን  ያስቆጠረ፣
             በኢኮኖሚ  መጠቃቀም  ላይ  የተመሰረተ  እንደመሆኑ  ዘለቂነት
             እንደሚኖረው  ይገመታል፡፡  ይሁንና  ጅቡቲ  ሃገሯን  በኢኮኖሚ

             አቅማቸው  ለጠነከሩ  የአካባቢ  የአረብ  ሀገራት  እና  ለሃያላን
             ሀገሮች በወታደራዊ የጦር ሠፈርነት እያከራየች በመሆኗ፣ ይህ
             ሁኔታ  ቀጥተኛ  የሆነ  እና  በቅርብ  ጊዜ  የሚፈፀም  ላይሆን
             ቢችልም፣  በረዥም  ጊዜ  ኢትየጵያን  ለማጥቃት  የሚፈልጉ
             ሃገሮች  ጅቡቲን  እንደመተላለፊያ  ሊጠቀሙባት  ስለሚችሉ፣


               33   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   30   31   32   33   34   35   36   37   38   39   40