Page 34 - አብን
P. 34
አብን
ከዚህ በተጨማሪ የቆየው የሱማሌ ብሔርተኝነት እና በምስራቅ
አፍሪካ ያሉ የሱማሌ ህዝብ የሰፈረባቸውን ልዩ ልዩ ግዛቶች
ወደ አንድ ለማሰባሰብ ያለ ህልመኝነት ጨርሶ ሊጠፋ ያልቻለ
የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ የስጋት ምንጭ ነው፡፡
ለ/ ደቡብ ሱዳን
በደቡብ ሱዳን ውስጥ ባሉ ዋና ዋና ጎሳዎች መካከል (ዲንካ
እና ኑዌር) ከነፃነቷ በኋላ የተቀጣጠለው የእርስ በርስ
ጦርነት፣ በጦርነቱ ሳቢያ ወደ ኢትዪጵያ የሚፈልሱ የደቡብ
ሱዳን ዜጎች መበራከት በኢትዮጵያ ላይ የኢኮኖሚ እና
የደህንነት ስጋት ፈጥሯል፡፡ በተለይም ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ
የሚፈልሱ በአብዛኛው የኑዌር ጎሳ አባላት መሆናቸው እና
ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ ወደ 450,000 የሚጠጉ በጋምቤላ
የሰፈሩ የደቡብ ሱዳን ኑዌሮች በኢትዮጵያ መንግስት ፈቃድ
ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዲፈቀድላቸው መደረጉ ወደፊት
የጋምቤላን ክልል ብሄረሰባዊ ጥንቅር በመቀየር ለኢትዮጵያ
ሃገራዊ ደህንነት የስጋት ምንጭ መሆኑ የማይቀይር ነው፡፡
ሐ. ሱዳን
በረዥም ጊዜ የጉርብትና ታሪካቸው ሱዳን እና ኢትዮጵያ
ወዳጅነት የፈጠሩበት ጊዜ በወያኔ ዘመን ነው ቢባል ከእውነቱ
መራቅ አይሆንም፡፡ ሱዳን የፖለቲካ እስልምናን በፖሊሲነት
መከተል የምትታወቅ መሆኗ ይህ ፖሊሲዋ የሚያቀራርባት
ከግብፅ እንጂ ከኢትዮጵያ ጋር ሊሆን አይችልም፡፡
32 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !