Page 43 - አብን
P. 43
አብን
ግብርና ምርታማነት እስከአሁንም ድረስ
ዝቅተኛ ነው፡፡
እስከዛሬ ድርስም በኢኮኖሚው የታየው
መዋቅራዊ ሽግግር ከግብርና ወደ አገልግሎት
ዘርፍ (የተለመዱ አገልግሎቶች) መሆኑም
ችግር ነው፡፡ መዋቅራዊ ሽግግሩ ወደ አምራች
ኢንዱስትሪ ወይም ወደ ዘመናዊ አገልግሎት
ዘርፍ (አይሲቲና ፋይናንስ) አለመሸጋገሩም
ከፍተኛ ችግር ነው፡፡
ከአስር ዓመት በላይ በተከታታይ የተመዘገበው
የኢኮኖሚ ዕድገት እያደገ የመጣውን የህዝብ
ቁጥርና ፍላጎትን በሚመጥን መልኩ አምራች
የስራ ዕድሎችን መፍጠር አልቻለም፡፡
እየወረደ የመጣ የገቢና የወጪ ምርቶች
አለመመጣጠንና መዛባት ያጋጠመ ሲሆን ከውጭ ገቢ
የሚደረገው ወደ ውጭ ከሚላከው ጋር ሲነጻጸር በአስር
ዓመታት ውስጥ ከእጥፍ ወደ 5.5 እጥፍ ሰፍቷል፡፡
ከፍተኛ የሆነ የዕዳ ጫናና ብድር የመመለስ አለመቻል
ዘላቂ አደጋ ያለ ሲሆን በ1994 ዓ.ም አገሪቱ ከነበረባት
72.6 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ዕዳ በስምንት ዓመት
ውስጥ በብዙ እጥፍ ጨምሮ በ2001 ዓ.ም ከ526.5
ቢሊየን ብር ደርሶ የነበር ሲሆን አሁን ላይ ከ2
ትሪሊየን ብር በላይ እንደደረሰ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
በ2010 ዓ.ም የሃገሪቱ እዳ አጠቃላይ የሃገር ውስጥ
ምርትን 61.11 በመቶ ደርሶ የነበር ሲሆን በያዝነው
የበጀት ዓመትም 58.51 በመቶ እንደሚሆን ይጠበቃል፡
41 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !