Page 46 - አብን
P. 46
አብን
የፖለቲካ ግንኙነት ያላቸውን የኢኮኖሚ ተዋንያኖች መረን
በለቀቀ ሁኔታ የሚያበለፅግ፣ “በነፃ ገበያ” ሽፋን በሃገር ላይ
የተጫነ የነገድ አባልነት የመጠቃቀሚያ መመዘኛ የሆነበት ነፃ
ያልሆነ (Crony Capitalism) የእድገት ሞዴል ነው፡፡
2.2. የግብርናው ዘርፍ እድገት መገታት
የሀገራችን ግብርና ከጠቅላላው ሕዝብ ወደ 85 ፐርሰንት
የሚሆነው የሰው ሃይል የተሰማራበት፣ ከጠቅላላው የሃገሪቱ
ምርት (GDP) ከአርባ እስከ 45 በመቶ የሚጠጋ ድርሻ
ያለው፣ 90 በመቶ ያህል የሃገሪቱን የወጪ ንግድ
የሚያበረክት በሃገር ውስጥ ላሉ አነስተኛና መካከለኛ
ኢንዱስትሪዎች 70 በመቶ ያህል የጥሬ እቃ ግብዓት
የሚሸፍን ነው፡፡ከላይ የሰፈሩት አሃዞች እንደሚያሳዩት
በሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ቁልፍ ሚና የሚጫወተው
የኢኮኖሚ ዘርፍ የዝናብ ጥገኛና ኋላቀር በሆነ የአመራረት
ዘይቤ የተተበተበ ነው፡፡ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ
አልቻለም፡፡ በግብርና የተሰማሩትን ገበሬዎች ለመቀየር ይቅርና
በዘርፉ የተሰማሩትን ገበሬዎች የምግብ ፍጆታቸውን
የማይሸፍን፣የከተማውን ነዋሪ የምግብ ፍላጎት በቅጡ
ለማሟላት ያልቻለ ዘርፍ ሆኗል፡፡ በሃገራችን በአሁኑ ወቅት
በየዓመቱ በአማካይ 10 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ለምግብ
እርዳታ ጥገኛ ሆኗል፡፡
ፈጣን ከሆነ የሃገሪቱ የህዝብ እድገት ቁጥር ጋር ሲነፃፀር
የገበሬው የነፍስ ወከፍ የመሬት ይዞታ ከግማሽ ሄክታር እያነሰ
መምጣቱ ፣ ከመሬት ለምነት እያሽቆለቆለ መምጣት ጋር
44 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !