Page 10 - አብን
P. 10
አብን
መድረክ ውስጥ የአማራ ህዝብ እንዳይደራጅና የመደራደር
አቅሙን እንዳያሳድግ የሚደረግ ሙከራ አፍራሽና በሸፍጥ
የተሞላ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡
በተጨማሪ የሀገራችን ብሄር ተኮር ፖለቲካ ከመነሻው ጀምሮ
ያለው ግንባርቀደም አንድምታ ለብዝሀነት እውቅና ለመስጠት
ሳይሆን የአማራን ህዝብ በጨቋኝነት ለመፈረጅ እንደሆነ ግልጽ
ነው፡፡ ስለሆነም የአማራ ህዝብ መደራጀት በመንግስት ውስጥ
በልኩ ለመወከልም ይሁን ለመከላከል የሚያስችለው መሰረታዊ
መነሻ እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡
የአማራ መደራጀት የጥላቻ ብያኔ ያነገበ አይደለም፡፡ ከሀገራዊ
ማዕቀፍ የማፈንገጥ ግብ የለውም፡፡ እንዲያውም የአማራ
ህዝብ መደራጀት ለጽንፈኞች የስጋት ምንጭ ሲሆን ለሀገር
ጥንካሬና አንድነት ደግሞ ሰፊ ዋስትና የሚሰጥ ነው፡፡ ይህ
በተግባር የተረጋገጠ ሀቅ ነው፡፡ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ/አብን/
ባለፉት አመታት ውስጥ ንጥል የሆኑ ድርጅታዊ
ፍጆታዎችንና የጥሬ ስልጣን ግብግቦችን ወደጎን በማለት ዘላቂ
ለሆነ የህዝብ ጥቅም፣ ለሀገር መረጋጋትና ደህንነት ቅድሚያ
በመስጠት ታሪካዊ ውሳኔዎችን እንዳስተላለፈ ይታወቃል፡፡
በዚህም ሀገራችንን ለጭቆና ወይም ለመፍረስ አደጋ ያጋለጡ
ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች እንዳይሳኩ ለማድረግ የበኩሉን
አይነተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡
አሸባሪው የትህነግ ሀይል ማዕከላዊ መንግስቱንና ሀገራችንን
ለማፍረስ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ
የተቀናጀ ጥቃት በከፈተበት ወቅት የአማራ ልዩ ሀይልና
8 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !