Page 4 - አብን
P. 4

አብን


             መሆኑ  የሚፈጸመውን  ጥቃትና  ያጠላውን  አደጋ  መቀልበስ

             ሳይችል  ቆይቷል፡፡  በኢትዩጵያዊነት  ስም  የተሰባሰቡ  ህብረ-
             ብሄራዊ  የፖለቲካ  ድርጅቶች  የአማራ  ህዝብን  ጥያቄዎች
             አውዳቸውን         በሳቱ     የዜግነት       መለኪያዎች         በመቃኘት፤
             ውስብስበና  ጥልቅ መነሻ ያላቸውን ጉዳዮች ወደ ታች እርከን
             በማውረድ  ተጨባጭ  እልባት  እንዳያገኙ  ተግዳሮት  ሆነው
             ቆይተዋል፡፡


             የአማራ  ህዝብ  እኩልነት፤  ፍትህንና  ዴሞክራሲ  እንዲሰፍኑና
             የሀገር ሉአላዊነትና አንድነት እንዲከበሩ ስለሚፈልግ ዝንባሌው
             “በአንድነትና  በዜግነት  ፖለቲካ”                ላይ  ሆኖ         እንዲቆይ
             አድርገውታል፡፡  ሆኖም  ይህ  ህዝቡን  በማንነቱ  እንዳይደራጅና

             ጥቃቶችን  እንዳይመክት  እንዲሁም  መሰረታዊ  ጥያቄዎቹን
             እንዳያስመልስ  መዘናጋት  ፈጥሮበት  እንደነበር  አይካድም፡፡
             “የአንድነት  ጎራ”  የሚባለው  ወጥ  የሆነ  ሀገራዊ  የጋራ  ግብ
             መሰነቅ  የማይችል፣  ጉልህ  የሆነ  የቅን  ልቦና  ጉድለት
             የሚስተዋልበት፣  አቅምና  ቁርጠኝነት  የሌለው  መሆኑ  ደግሞ
             ችግሩን አባብሶት ቆይቷል፡፡


             የጥላቻ ሃይሎች ቁጥር እየጨመረና አቅማቸው እየጎለበተ ሄዶ
             በህዝቡ  ላይ  ለዘመናት  በከፈቱት  የመፈረጅ፤  የማግለልና

             የማጥቃት  ተግባራት  በህዝባችን  ላይ  የህልውና  አደጋ
             ፈጥረዋል፡፡ የአማራ ሕዝብ እስካሁን ድረስ ያልተቋረጡ የዘር
             ማጥፋት ወንጀሎች እየተፈጸመበት ይገኛል፡፡ በተያያዘ መልኩ
             በታቀዱና  በተቀናጁ  ጥቃቶች  ምክንያት  የሚደርሱበትን
             ዘርፈብዙ  ጉዳቶች  ከዘገባ  ውጭ  ማድረግ  እውቅና  የመንፈግ
             ስልታዊ አሻጥሮች ተፈጽመውበታል፡፡

                2   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   1   2   3   4   5   6   7   8   9