Page 12 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 12

አብን


             በተለይም  የአማራን  ህዝብ  በጠላትነት  መፈረጅ  የጥላቻ

             ሀይሎች  ሁሉ  የጋራ  ቆጣሪ  ከመሆን  አልፎ  የመንግስት
             መዋቅር  የማደራጃ  መርህ  ለመሆን  በቅቷል፡፡  የዜሮ  ድምር
             ፖለቲካው  ተዋንያን  በስትራቴጂና  በታክቲክ  መካከል  ሊኖር
             የሚገባውን        መሰረታዊ         ልዩነት      መገንዘብ       አቅቷቸዋል
             በሚያስብል ደረጃ መርህ አልባ እንቅስቃሴንና አደረጃጀትን ግብ
             ሲያደርጉ ተስተውሏል፡፡ የአማራን ህዝብ ማጥቃትና ማዳከም
             ከታክቲክነት  አልፎ  መዳረሻ  ግብ  ተደርጎ  እንደተወሰደ  ማየት
             ይቻላል፡፡  ሆኖም  አማራውን  ለመጉዳት  የነበራቸው  ፖለቲካዊ

             ሴራ ዳፋው እንወክለዋለን ለሚሏቸው ህዝቦች ጭምር ሊተርፍ
             እንደቻለ ታይቷል፡፡


             የተፎካካሪውን  ጎራ  ጨምረን  ስንመለከት  አብዛኛው  የትግል
             ዘመን  የባጀው  አደረጃጀትን  ግብ  አድርጎ  በመውሰድ፤  ነባር
             ሀገራዊ  እሴቶችን  በመንቀል  እንዲሁም  በሀገሪቱ  መሬት  ላይ
             ባዕድ  ዘር  በመበተን  ነበር፡፡    ከቅርብ  ጊዜ  ወዲህ  ደግሞ
             ተሸናፊነቱን  የሚያሳብቅ  “የተረኞች”  ምርኩዝ  በመሆን
             የሚፈለገው  ዘላቂና  አስተማማኝ  ለውጥ  እውን  እንዳይሆን

             በችግር  ፈጣሪነት  ተሰልፏል፡፡  በአምባገነኖች  ቀለምና  ዘር  ላይ
             የተመሰረተ          የተቃውሞና           የድጋፍ        እንቅስቃሴዎችን
             በመመልከት  እስካሁን  ለምን  ሀገራችን  ከጭቆና  ቀንበር
             መላቀቅ እንዳልቻለች እንረዳለን፡፡


             በተለምዶ  የመርህም  ይሁን  የሀገራዊ  ቅጽሎችን  መጠሪያቸው
             ያደረጉ  በርካታ  እንቅስቃሴዎችና  አደረጃጀቶችን  በመገምገም
             ሀገርንና  ህዝብን  ለመታደግ  በማያስችል  የቃላት  ድርደራ



               10   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   7   8   9   10   11   12   13   14   15   16   17