Page 15 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 15

አብን


             ንቅናቄያችን  የኮሮና  ወረርሽኝ  መከሰቱን  መነሻ  በማድረግ

             በሀገራችን  ታቅዶ  የነበረውን  ምርጫ  በተመለከተ  አቋም
             መውሰዱ  ይታወሳል፡፡  አብን  ምርጫው  መተላለፍ  አለበት
             የሚል ውሳኔ ሲያሳልፍ በዋናነት አማራ ጠል ጽንፈኛ ሀይሎች
             በቅንጅት  የማእከላዊ  መንግስት  ስልጣንን  በመቆጣጠር
             ህዝባችንንና  ሀገራችንን  ለዳግም  ጥቃትና  ጭቆና  ሊዳርጉ
             የሚችበት እድል መዘጋት አለበት የሚል አቋም በመያዝ ነበር፡
             ፡ በተጨማሪ የምርጫውን ጊዜ በማስተላለፍ በመካከል አንኳር
             የሆኑ  የእሳቤና  የመዋቅር  ሪፎርሞች  እንዲደረጉ፣  ለዚህም

             የብሄራዊ  ውይይትና  ድርድር  መድረኮች  እንዲከፈቱና  ዘላቂ
             እልባቶች  እንዲፈለጉ  የሚሉ  ማሳሰቢያዎችን  በማቅረብ
             አጠቃላይ  ሀገራዊ  አስቻይ  ሁኔታዎች  እንዲፈጠሩ  በሚል
             ነበር፡፡ በመካከል ትህነግን ጨምሮ ጽንፈኛ ሀይሎች ከማዕከል
             የተገፉበትን  ምእራፍ  ለመክፈት  ተችሏል፡፡  የአብን  ፖለቲካዊ
             አቋም  ለጽንፈኞቹ  መገፋት  ወሳኝ  አስተዋጽኦ  እንደነበረው

             አይካድም፡፡  ሆኖም  የብሄራዊ  ውይይትና  ድርድር  መድረኮች
             እውን ሊሆኑ ባለመቻላቸው ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጡ የሚችሉ
             ለውጦችን መከወን አልተቻለም፡፡ ይህ ምእራፍ ቀጣዩ የአማራ
             ሕዝብና እንደ ድርጅት የአብን የፖለቲካ ስምሪት የሚደረግበት
             ይሆናል ማለት ነው፡፡


             የአማራ  ብሔራዊ  ንቅናቄ  (አብን)  6ተኛውን  ሐገር-አቀፍና
             ክልላዊ  ምርጫ  በተሳካ  ሁኔታ  ለመምራት  እና  በድል
             ለማጠናቀቅ  የሚያስችለውን  ስትራቴጂ  ነድፎ  የተጠናከረ
             እንቅስቃሴ  በማድረግ  ላይ  ይገኛል፡፡  ምንም  እንኳ  አብን
             ሀገራዊው  የፖለቲካ  ቅድመ  ምርጫ  መደላድል  የሌለው

             መሆኑን  ቢረዳም፣  ከምርጫ  በፊት  ሀገራችን  ከጥላቻ  ትርክት
               13   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   10   11   12   13   14   15   16   17   18   19   20