Page 20 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 20

አብን




                                       ክፍል አንድ
                                የነባራዊ ሁኔታ ግምገማ
               በስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ የአመለካከት መዛባትና የተግባር
                                         ክሽፈት

               1.     የፖለቲካ ችግሮች
             1.1.  ሃገሪቱ ከአገዛዝ ወደ ዲሞክራሲ ለመሸጋገር የጀመረችው
                    ጉዞ መጨናገፍ

             ከአገዛዝ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመሸጋገር በስልጣን ላይ

             ያለውን  መንግስታዊ  ስርዓት  ዋና  ዋና  ገጽታዎች  መለወጥ
             (political  Liberalization)  ያስፈልጋል፡፡  አገዛዙ  ሲጠቀምበት
             ከነበረው  ሕገመንግስት  ጀምሮ  ለጭቆናው  ሲገልገልባቸው
             የነበሩ  መዋቅሮች፣  አፋኝ  ህግጋቶችን  እና  ደንቦችን  መቀየርና
             ማስተካከል ይጠይቃል፡፡


             ከነዚህም በተጨማሪ እንደመከላከያ፣ ደህንነት እና ፖሊስ ያሉ
             ተቋማት  ከገዥ  ፓርቲው  ገገልተኛ  ሆነው  የሚሰሩበት  ሁኔታ
             ሊመቻች  ይገባል፡፡  የፍትህ  ስርዓቱም  ገለልተኛነት  መከበር
             በሽግግሩ የመጀመሪያ ወቅት  መከናወን ያለበት ተግባር  ነው፡፡
             ከአገዛዝ ወደ ዲሞክራሲ የሚደረግ ሽግግር ሁለተኛው ምዕራፍ
             ደግሞ  የዲሞክራሲ  ሂደቱን  የማስፋት  እና  የማጠናከር  ሂደት
             (Democratization)  ሲሆን፣  ይህ  ሂደት  ነፃ  የፖለቲካ  እና

             የሲቪል ተቋማት የሚገነቡበት ሂደት ነው፡፡

             በጠቅላይ  ሚ/ር  አብይ  የሚመራው  መንግስት  ወደ  ስልጣን
             ሲመጣ  የአብዛኛው  የሃገሪቱ  ሕዝብ  ድጋፍ  ቢቸረውም፣


               18   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   15   16   17   18   19   20   21   22   23   24   25