Page 8 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 8
አብን
በአማራ ህዝብ ሊሆን እንደሚገባ ግንዛቤ ፈጥሯል፡፡
በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ውስጥ የአማራን ህዝብ መሰረታዊ
ጥያቄዎች በአግባቡ ለመመርመር፤ ለመገንዘብና እልባት
ለመሻት እሰራለሁ የሚል አካል ከመነሻው የተሟላ ፍላጎት
ያለው፣ ተገዳዳሪና የሚመጥን አቅም ማጎልበት የሚችል
ሊሆን ይገባል፡፡ በመሰረቱ ይህ እውን ይሆን ዘንድ አማራዊ
ማንነትንና አርበኝነትን መርህ ያደረጉ አደረጃጀቶችን
መፍጠርና ማዋቀር ወቅቱ የሚጠይቀው እንቅስቃሴ ሲሆን
ብቸኛውና አዋጩ የፖለቲካ ፍኖት መሆኑንም በአጽንኦት
መቀበል ይገባል የሚል ጠንካራ አስተሳሰብ ነው፡፡ እስካሁን
ድረስ የአማራ ህዝብ ትግል ሀሳባዊ በሆነ የአንድነት ፖለቲካ
የተቃኘ በመሆኑ ጠላቶቹን መመከት እንዳይቻል ከማድረግ
ባለፈ በህዝቡ ላይ የተነዙት ስሁት ትርክቶችን ለማረጋገጥ
በማስረጃነት ሲጠቀስ ቆይቷል፡፡ በዚህ ምክንያት ህዝቡ
ለከፍተኛ ኪሳራና ማህበራዊ ምስቅልቅል ሊዳረግ ችሏል፡፡
በሂደት የአማራ ህዝብ በማንነቱ መደራጀት እንዳለበት
እየታመነ መምጣቱና በተለይም በልሂቃኑ በኩል የተቸረው
ከፍተኛ ድጋፍ ተቀባይነቱ በፍጥነት እንዲጨምር አስተዋጽኦ
አድርጓል፡፡ በተቃራኒው አማራን በጠላትነት በፈረጁ ሃይሎችና
ዋና የድጋፍ መሰረታቸውን በአማራ ህዝብ ላይ በጣሉ
ሃይሎች ላይ ስጋት ፈጥሮ ቆይቷል፡፡ በዚህም ሰፊ ለሆነ
ወከባ፣ ውግዘትና ፍረጃ አልፎ አልፎም ለጥቃት ተጋላጭ
በማድረግ የመቀልበስ ሙከራዎች ተደርገዋል፡፡ ሆኖም የአማራ
ህዝብ በኑሮ ተሞክሮ ራሱ ያረጋገጣቸውን ሀቆችና በማንነቱ
ተደራጅቶ ግቦቹን ለማሳካት የሚያስችለውን ብቸኛና አዋጭ
ንቅናቄ አጠናክሮ ለመጓዝ ሰፊ ማህበራዊ መግባባት እንደፈጠረ
6 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !