Page 6 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 6

አብን


             ሕዝብ ድርጅት (መአሕድ) ለማፍረስ በወቅቱ ተከፍተው የነበሩ

             የሴራ ጥቃቶች አይተኛ ማሳያ ሆነው የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

             ከመአሕድ  መመስረትና  እንቅስቃሴ  ጋር  ተያይዞ  እየጎለበተ

             የመጣዉን  የአማራ  ህዝብ  የመሰባሰብና  የመደራጀት  ዝንባሌ
             በተሟላ  መልኩ  ለማስተጓጎል  የአማራ  ጠል  ልሂቃንን
             ከየአቅጣጫው በውጭጭ በመሰብሰብ ብአዴን የሚባል ድርጅት
             ተሰርቶ  በህዝባችን  ትክሻ  ላይ  በጭቆና  ቀንበርነት  ተጭኖ
             ቆይቷል፡፡  በዚህ  መልኩ  በተተገበረው  የሴራ  ጥልፍልፍ
             አማካኝነት  በአማራ  ህዝብ  ላይ  የሚፈጸመውን  የፍረጃ፣
             የማግለል፣  የመግፋትና  የማጥቃት  ፖለቲካዊ  አላማ  የተሟላ
             ስኬት  እንዲኖረው  ለማድረግ  ተሞክሯል፡፡  የአማራ  ህዝብ

             ለበርካታ  አስርት  ዓመታት  በተከፈቱበት  ጥቃቶች  ለመጠነሰፊ
             የመፈናቀል፣  የጅምላ  ፍጅት፣  የንብረት  መውደምና  የስነልቦና
             ቀውስ ሰለባ እንዲሆን የማድረግ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡


             በተጨማሪ  የአማራን  ህዝብ  ማህበራዊ  ዕረፍት  ለመንሳትና
             ለወደፊት  ሀገራዊ  የፖለቲካ  ሀይል  መሆን  እንዳይቸል
             ለማድረግ  የታለሙ  በርካታ  ሴራዎች  ተፈጽመዉበታል፡፡
             በሀገራችን  የተለያዩ  አካባቢዎች  የሚኖረው  የአማራ  ህዝብ
             በግንባር  ቀደም  የሰብዓዊ  መብቶቹን  እንዲገፈፍና  የማንነት

             መገለጫዎቹን ጭምር እንዲነጠቅ ተደርጓል፡፡ የአማራን ህዝብ
             በጨቋኝነት  የፈረጀው  ትርክት  በተሟላ  መልኩ  ተግባራዊ
             የተደረገው  በተለይ  ‘አማራ  ክልል’  ተብሎ  ከሚጠራው  ውጭ
             በሚኖረው  አማራ  ላይ  መሆኑ  አይዘነጋም፡፡  ህዝባችን  አብሮ
             ባቀናው፤ ተወልዶ ባደገበትና አብሮ በኖረበት ነሃገሩና በቀየው
             ሁሉ  “ነፍጠኛና  ትምክህተኛ”፣  ‘ጨቋኝ’፤  ‘መጤና  ወራሪ’

                4   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   1   2   3   4   5   6   7   8   9   10   11